Friday, December 13, 2024
Google search engine
HomePolitics“ሩሲያ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ኅብረት በኩል የሚደረገውን ድርድር ትደግፋለች”፡- ሰርጌይ ላቭሮቭ

“ሩሲያ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ኅብረት በኩል የሚደረገውን ድርድር ትደግፋለች”፡- ሰርጌይ ላቭሮቭ

“ሩሲያ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በአፍሪካ ኅብረት በኩል የሚደረገውን ድርድር ትደግፋለች”፡- ሰርጌይ ላቭሮቭ 
 

ሩሲያ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ያላቸውን ልዩነት በአፍሪካ ኅብረት መሪነት አንዲፈታ ድጋፍ እንደምታደርግ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ለቭሮቭ አስታውቀዋል።

ለሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ግብፅ የገቡት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ለቭሮቭ፣ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በንግድ እና በሌሎችም ርዕሰ ጉዳዮች ከግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ እና ከግብፁ አቻቸው ሳሜህ ሹክሪ ጋር ተወያይተዋል። 

ሚኒስትሩ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ሦስትቱን አገራት እንድታደራድር ለሩሲያ ግብዣ ያልቀረበላት ቢሆንም ለዓመታት ከስምምነት ያልደረሰበትን ድርድር ውጤታማ ለማድረግ በአፍሪካ ኅብረት መሪነት ለሚካሄደው ድርድር የሩሲያ መንግሥት ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ከግብፅ መሪዎች ጋር የመከሩት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ወደ ኢራን ማቅናታቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።

Source:EBC

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments