Friday, March 29, 2024
Google search engine
HomeBAWZA NEWSየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያዘጋጀው የጸሎተ ሀሙስ እና የረመዳን የኢፍጣር መርሐግብር ተካሄደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያዘጋጀው የጸሎተ ሀሙስ እና የረመዳን የኢፍጣር መርሐግብር ተካሄደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያዘጋጀው የጸሎተ ሀሙስ እና የረመዳን የኢፍጣር መርሐግብር ተካሄደ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጸሎተ ሀሙስ እና የረመዳን የኢፍጣር መርሐግብር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት አቡነ ፍሊጶስ ፣የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እንድሪስ ፣የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ጻዲቁ አብዶ እና የሁሉም ሀይማኖት ተቋማት መሪዎች እና የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በስካይላይት ሆቴል ሆቴል ተካሂዷል ።

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በመርሃግብሩ እንደገለፁት ኢትዮጵያ የተለያዩ ሀይማኖቶች ፣ብሄሮች እና ቋንቋዎች ሳያለያዩ እንደሰርገኛ ጤፍ አንድ የሆኑባት ድንቅ ሀገር ነች።

እኛ ኢትዮጵያዊያን አንድ ሀገር፣አንድ ስነልቦና ያለን አብሮነታችችነና አንድነታችን ለአለም ምሳሌ የሆንን ህዝቦች ነን ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ይህ መቻቻል እና መከባበር ለአንድነታችን እና ለታላቅነታችን መሰረት በመሆኑ ተጠናክሮ እና ዳብሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል ።

ይህን የመቻቻል እና የመከባበር እሴት በማዳበር በኩል የሀይማኖት አባቶች ሚና ትልቅ በመሆኑ በየቤተእምነታቸው ለምእመኑ የመከባበርና መቻቻል እሴታችን እንዲዳብር መስራት እንደሚገባ ምክትል ከንቲባዋ ጠቁመዋል ።

በመርሐግብሩ ላይ የየሀይማኖት ተቋማቱ መሪዎች ስለሰላም፣ስለአብሮነት ፣አንድነት እና መቻቻል መልዕክት አስተላልፈዋል ።

EBC

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments