Friday, April 19, 2024
Google search engine
HomeTechnologyየዩኒቨርሲቲዎቻችን አሁናዊ ተግዳሮቶችበሚል ረዕስ በዶ/ር ታፈረ መላኩ የተጻፈው መጽሐፍ በደማቅ ስነ-ስርዓት በየጎንደር...

የዩኒቨርሲቲዎቻችን አሁናዊ ተግዳሮቶችበሚል ረዕስ በዶ/ር ታፈረ መላኩ የተጻፈው መጽሐፍ በደማቅ ስነ-ስርዓት በየጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመረቀ።

የዩኒቨርሲቲዎቻችን አሁናዊ ተግዳሮቶችበሚል ረዕስ በዶ/ር ታፈረ መላኩ የተጻፈው መጽሐፍ በደማቅ ስነ-ስርዓት በየጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመረቀ።

በምረቃ ስነስርዓቱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የሚዲያ ተቋማት ተገኝተዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር አስራት አጸደወይን በንግግራቸው የምረቃ ስነ-ስርዓቱን የከፈቱ ሲሆኝ”መሪ ሆኖ በቆራጥነት ለአገርና ለተቋማት የመውጫ መንገድ አመላካች መጽሐፍ ማዘጋጀት ዶ/ር ታፈረን ከመሳሰሉ ቅን አሳቢና ደፋር ሰዎች የሚጠበቅ መሆኑን በመናገር ለደራሲው እኖኳን ደስ አለህ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ዶ/ር አስራት አያይዘውም በዚህ ወቅት ዩኒቨርሲቲዎችን መምራት በርካታ ውስብስብ ፈተናዎች የበዙበትና አስቸጋሪ መሆኑን በማውሳት ሁሉም የዩኒቨርስቲ አመራሮች የገጠመንን ፈተና እና የዩኒቨርሲቲዎች ተግዳሮት በመጽሐፍ መልኩ መውጣቱ ለችግሮች መፍትሄ ለመስጠትና መውጫ መንገዶችን ለመዘየድ፣ በተለይም ለዩኒቨርስቲ አመራሮች፣ ተጠሪ መስሪያ ቤቶችና ለማህበረሰቡ እጅግ ጉልህ ፋይዳ ያለው መጽሃፍ መሆኑን ተናግረዋል። ከመጽሐፉ አግራሞት ያጫረባቸውን ገጾች በማንበብም ለታዳሚው ገለጻ አድርገዋል።

የዩኒቨርሲቲዎቻችን አሁናዊ ተግዳሮት የተሠኘው መጽሐፍ በወፍ በረር ታሪኩንና ጭብጡን ለታዳሚው አቶ ግርማው አሸብር ያቀረቡ ሲሆን  ሁለት ምሁራን በመጽሐፉ ላይ ትንታኔያዊ ዳሰሳ ያደረጉ ሲሆን ለመነበብ እና ለስሜት ቅርብ የሆነ ቋንቋዊና ስነጽሁፋዊ ውበቱ ከጭብጡ አንጻር ይበል የሚያስብል መጽሐፍ መሆኑን ተናግረዋል።

የመጽሀፉ ደራሲ ዶ/ር ታፈረ መላኩ የጎንደር ዩኒቨርሲቲን በማመስገን መጽሐፉን ለማዘጋጀት ያነሳሳቸው ዋናው ቁምነገር በሀገራዊ ፖለቲካዊ ሁኔታው በዩኒቨርሲቲዎች ላይ እያሳደረ ያለው ጫና በነገ አገር ተረካቢ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ያሳረፈውን ችግር ለመታዘብ እሳቸው የተቋም መሪ መሆናቸው ጉዳዩን እንዲያጤኑት ኤድል የሰጣቸው ስለሆነ መሆኑን ተናግረዋል። ተቋማት ከማንኛውም ፖለቲካዊ ተጽዕኖ ተላቀው ለተቋቋሙበት ዓላማ አገርን በማልማትና ትውልድን በመቅረጽ መስራት እንዳለባቸው ያላቸውን ጽኑ እምነት ተናግረዋል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደኔት ዶ/ር አስራት አጸደወይን ከሁለቱ የዘርፍ ምክትል ፕሬዚዳንቶቻቸው ጋር በመሆን መጽሐፉን በደማቅ ስነስርዓት መርቀዋል

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments