Friday, March 29, 2024
Google search engine
Homeወደ ሀገር ዉስጥ ሊገባ የነበረ ከመቶ ሰማንያ ሺህ በላይ የእጅ ገጀራ በቁጥጥር...

ወደ ሀገር ዉስጥ ሊገባ የነበረ ከመቶ ሰማንያ ሺህ በላይ የእጅ ገጀራ በቁጥጥር ስር ዋለ::

ወደ ሀገር ዉስጥ ሊገባ የነበረ ከመቶ ሰማንያ ሺህ በላይ የእጅ ገጀራ በቁጥጥር ስር ዋለ::ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 18/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ከ15 ቀን በፊት በአስመጪ ዳዊት የማነ ስም ብዛቱ 186 ሺህ 240 የእጅ ገጀራ በአራት ባለ 20 ጫማ ኮንቴይነሮች ከቻይና ተጭኖ ሞጆ ጉምሩክ ተጓጉዞ ከደረሰ በኃላ እቃው በዲክላራሲዮን ቁጥር 4-1919/21 ተመዝግቦ ወደ ሀገር ዉስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ የተፈቀደለት በማስመሰል ነው ሊገባ ሲል የተያዘው፡፡

እቃው እንዲገባም ሐሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ ለገቢ ዕቃ አወጣጥ የሰነድ መርማሪ አቅርቦ ሰነዱ ተመርምሮ ከ7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ቀረጥና ታክስ ከፍሎ ከተለቀቀ በኃላ በጉምሩክ ኮሚሽን እና በሞጆ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኢንተለጀንስ በተደረገ ክትትል ሰነዱ ሐሰተኛና እቃዉም ወደ ሀገር ዉስጥ እንዲገባ ከፌዴራል ፖሊስ ፈቃድ ያልተሰጠው መሆኑ ተረጋግጧል::አስመጪው ያቀረብኩት ሰነድ ሕጋዊ ነው በማለት ቅሬታ ቢያቀርብም ሰነዱ ሐሰተኛ እና ከፌደራል ፖሊስ ፍቃድ ያልተሰጠው መሆኑን ነው የገቢዎች ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ የገለጸው ፡፡

በተጨማሪም በጉምሩክ ኮሚሽን ሠራተኛ የእጅ ገጀራው ተገቢውን የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት በመፈጸም እንዲስተናገድ የሚገልጽ ሐሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ለማውጣት ቢሞከርም ሐሰተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ለሞጆ የወንጀል ምርመራ ማስተባባሪያ ጽሕፈት ቤት መረጃዉን በመስጠት በተደረገ ክትትል የእቃው ባለቤት እና አስተላላፊው ተይዘው ጉዳዩ በምርመራ ላይ ይገኛል:: ገጀራ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ክልከላ ከተደረገባቸው ዕቃዎች አንዱ ነው፡፡ በአንዳንድ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች በጉምሩክ ኮሚሽን ባለሙያ እቃው እንዲወጣ የተፈቀደበት ደብዳቤ በማስመሰልና ሐሰተኛ የደብዳቤ ፎቶ በመጠቀም አስመጪው ሕጋዊ እንደሆነ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments