Friday, March 29, 2024
Google search engine
HomeLifestyleበጎረቤቱ የጨከነ ለቤተሰቡ አይራራም (በእውቀቱ ስዩም)

በጎረቤቱ የጨከነ ለቤተሰቡ አይራራም (በእውቀቱ ስዩም)

በጎረቤቱ የጨከነ ለቤተሰቡ አይራራም(በእውቀቱ ስዩም)

እንዳነበብኩት ከሆነ ፥ የኦሮሞ ብሄረሰብ ” የቱለማ ኪዳን “ የሚባል በጎ ባህል ነበረው ፤ በዚህ ባህል መሰረት አንድ ባይተዋር ሰው (ዘሩ ምንም ይሁን ምን) በማህበረሰቡ ውስጥ ገብቶ የሙጥኝ ካለ ህዝቡ ጥበቃ ያደርግለታል፤ ጠላት ቢያሳድደው ይመክትለታል፤ ከሆነ ዘመን ወዲህ ፥ በጦርነት ሜዳ ላይ ከጠላት ጎራ ሴት እና ብላቴኖች ከተገኙ ተማርከው ይጋዛሉ እንጂ አይገደሉም ፤ እንዲሁም በጦርነት ወቅት ሴት አትገደልም፤” ሴት የገደለ ቅቤ የለም( አይቀባም) ይሳቅበታል “ ይላሉ ታሪክ ፀሀፊው አለቃ አጥሜ ፤ የመንፈሳዊ አባት መግደልም ነውር ነበር፤ እኒህ የጦርነት ደንቦች ህጎች ባንዳንድ አጋጣሚዎች ቢጣሱም ጠቅላላ ህጉ አልተናጋም::

አሁን በዘመናችን በኦሮምያ ክልል ባንዳንድ ቦታ በየጊዜው የሚደረገው ሁሉ እንዲህ እንዲህ አይነቱን ባህል ባፍጢሙ የሚደፋ ነው ፤ ጦርነት በሌለበት ፤ ወንድ ሴት ሳይሉ መደዳውን መፍጀት የወትሮ ዜና ሆኗል ፥ አብሮ የኖረ፥ ጎረቤትን ከመሬቱ ከንብረቱ መንቀል ተለምዷል! ፤ ያልተሰራ ግፍ ያልታየ የጭካኔ አይነት የለም፤ ይህ ከባህላችን እና ከመንፈሳዊ ቅርሳችን ጋር አይሄድም ብሎ ድምፁን የሚያሰማ ሽማግሌ ጠፋ !ጭራሽ በተገላቢጦሽ የተበዳይን ጩኸት መቀማት ሰፈነ፤ ምንድነው? ምን ጉድ ወረደ? ህሊና ፤ ፈጣሪን መፍራት የት ሄደ? ግዴለም ለሌላው ህዝብ ማሰብ ይቅር ፤ ከዘመዶቼ ውጭ ያለው ህዝብ ህልውና አይመለከተኝም የሚል ሰው እንኳ እንዲህ አይነቱ ነገር ይበጀዋል? የገዛ ባህሉን ምሶሶዎች ሲወድሙ ዝም ብሎ የሚያይ ህዝብ ራሱን እያጠፋ ነው ፤በክልልህ ስርአት አልበኝነት ከነገሰ ዙርያ ገባው አምርሮ ይጠላሀል፤ ባልሞትባይ ተጋዳይነት በየአቅጣጫው ይዘምትብሀል፤ በሰፈርህ መስራት፤ መነገድ ኢንቨስት ማድረግ የሚፈቅድ አይኖርም፤ ቀስበቀስ ስራአጥነት ይነግሳል፤ ዛሬ ጎረቤትህን ሲገድልና ሲመዘብር ዝም ያልከው ጎረምሳ ልጅህ ነገ በትሩን ባንተ ላይ ያነሳል ፤ በጎረቤቱ የጨከነ ፥ ለቤተሰቡ ይራራል ብለህ ካሰብክ ተሳስተሃል፤ እስከ መቼ መከራ እስኪመክረን እንጠብቃለን? አንዳንዴ እንኩዋ ከሌሎች አገሮች መከራ እንማር እንጂ፤

Bewketu Seyoum

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments