Thursday, March 28, 2024
Google search engine
HomeLifestyleአንዳንድ ጊዜ ሀገር አርብ ላይ ትሆናለች!

አንዳንድ ጊዜ ሀገር አርብ ላይ ትሆናለች!

አንዳንድ ጊዜ ሀገር አርብ ላይ ትሆናለች!!

(ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት)

አርብ አዳም እየዳነ ነው ፡፡ ነገር ግን ክርስቶስ አየተገረፈና እየተሰቀለም ነው ፡፡ ፀሐይ ጨለማለች ፣ ጨረቃ ደም ለብሳለች ፣ ምድር ትንቀጠቀጣለች ፣ ሐዋርያት ሸሽተዋል መጻጉእ በሐሰት መስክሯል ጲላጦስ የእውነት ፍርድ ለመፍረድ ተቸግሯል ፡፡

በጥብርያዶስ ባሕር ሲበላ < ካልነገሥክ > ያለው ሕዝብ ተገልብጦ ካልተሰቀለ እያለ ነው ያቺ ቀን የክርስትና የመጨረሻዋ ቀን ትመስል ነበር ፡፡ የክርስቶስ ሆኖ የተገኘ ሁሉ ይቀጠቀጣል ፡፡ ለዚህም ነበር ወጣቱን ማርቆስን ያባረሩት ፡፡

ሐናና ቀያፋ ጉልበት አግኝተዋል የጭካኔአቸውን ልክ ሁሉ እያወረዱት ነው ፡፡ ዮሐንስ ያለቅሳል ፣ እመቤታችን በኀዘን ቆማለች ሁሉም ነገር ያበቃና የተቆረጠ መስሏል ፡፡ በዚህ መካከል ግን የሚነሱ ሙታን ነበሩ ፣ የሚቀደድ የጥል መጋረጃ ነበር ፣ ፈያታዊ ዘየማን ገነት እየገባ ነበር ፣ ዮሐንስ ለእመቤታችን ልጅ ሆኖ እየተሰጠ ነበር ፣ የጲላጦስ ሚስት ስለእውነት እየመሰከረች ነበር ፡፡

ሮማዊው መቶ አለቃ ስለክርስቶስ እውነቱን እየተናገረ ነበር ፡፡ ግን እነዚህን ጣፋጭ ድምጾች ሌሎች የክፋትና የጨለማ ድምጾች ውጠዋቸው ስለነበር በቂ ሰሚ አላገኙም ፡፡ በቂ ሰሚ ያገኙት በኃላ ነው ፡፡ ሀገርም እንዲ ትሆናለች አርብ ላይ ስትሆን ፀሐይ የጨለመባት ፣ ጨረቃም ደም የለበሰችባት ትመስላለች ፡፡ መድኃኒት አልባ ፣ ተስፋ አልባ ትመስላለች ፡፡

ወንጀለኞች ደስታ ተጎናፅፈው ንጹሐን መስቀል ሥር ያለቅሳሉ ፡፡ ትናንሽ ጭላንጭሎችን የሚያያቸው ጥቃቅን ብርቱ ድምጾችን የሚሰማቸው ያጣሉ ፡፡ ሁሉም የዋጠውን ጨለማ እንጂ የተሰቀለውን ብርሃን አያይም ፡፡ ግን አርብ ያልፋል ቅዳሜም ይነጋል እርሱም በዝምታ ይመሻል እሁድም ይደርሳል ፡፡

ትንሳኤም ይመጣል አርብም በእሁድ ትተካለች ፡፡ከአርብ ወደ እሁድ ለመሻገር ግን እንደ እመቤታችንና እንደ ዮሐንስ ያሉ ፅኑዓንን ይፈልጋል ፡፡

ዛሬ ኢትዮጵያ አርብ ላይ ናት ግን በቅዳሜ በኩል ተሻግራው እሁድ እንደምትደርስ እናምናለን ፡፡

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments