Saturday, April 20, 2024
Google search engine
HomePoliticsበኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አውደ ጥናት እና አውደ ርእይ ተከፈተ::

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አውደ ጥናት እና አውደ ርእይ ተከፈተ::

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አውደ ጥናት እና አውደ ርእይ ተከፈተበኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሰው ሰራሽ አስተወሎት (የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ) አውደ ጥናት እና አውደ ርእይ በአዲስ አበባ ከተማ ተከፍቷል።

ለዓለምዓቀፉ ማህበረሰብ ሀገርኛ ቋንቋዎችን ተደራሽ ለማድረግ አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ እና ትግርኛን ቋንቋዎችን ከማሽኖች ጋር የማስተዋወቅ ስራ ተጀምሯል ተብሏል።በመድረኩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብረሃም በላይ በበኩላቸው የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሰው ሰራሽ አስተወሎት ማእከሉ ሚናው የላቀ ነው ብለዋል።

በተዘጋጀው አውደ ጥናት እና አውደ ርእይ ላይም ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ለዘርፉ ቅርበት ያላቸው ከፍተኛ ተቋማት እና ተመራማሪዎች ተሳትፈውበታል።“የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው አውደ ርእይ እስከ ሚያዚያ 10 በኢንተርኮነቲኔንታል ሆቴል ይቀጥላል ተብሏል።አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ማእከል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና በመድረኩ መክፈቻ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ለሁሉም ዘርፎች አስፈላጊ ቢሆንም ባለው አቅም ልክ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የምትፈልገውን ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚያስችል አቅምን ለመገንባት ያግዛልም ነው ያሉት ዶ/ር አብረሃም።በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሃሳብ አመንጪነት የተከፈተው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማእከል ከመስከረም ወር ጀምሮ በይፋ በስራ ላይ ይገኛል። ማእከሉ በዋናነት በሃገር ደረጃ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምር እና ልማት ማእከልን በማቋቋም የዲጂታል ዳታ ክምችትን የማደራጀት ስራን እየሰራ ነው።

ምንጭ: ኢቢሲ

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments