Thursday, March 28, 2024
Google search engine
HomePoliticsየተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ ክልል የተደረገውን የህግ ማስከበር ዘመቻን...

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ ክልል የተደረገውን የህግ ማስከበር ዘመቻን ተከትሎ የተፈጠረውን ሰብአዊ ቀውስ ለማረጋጋትና ሰብአዊ ድጋፎችን በማቅረብ ኢትዮጵያ ላደረገችው ጥረት እውቅና ሰጥቷል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በትግራይ ክልል የተደረገውን የህግ ማስከበር ዘመቻን ተከትሎ የተፈጠረውን ሰብአዊ ቀውስ ለማረጋጋትና ሰብአዊ ድጋፎችን በማቅረብ ኢትዮጵያ ላደረገችው ጥረት እውቅና ሰጥቷል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያን በሚመለከት የፕሬስ መግለጫ አውጥቷል። ሰብአዊ ድጋፎችን ለተረጂዎች ለማድረስ ፈታኝ ነገሮች ቢኖሩም ኢትዮጵያ መንግስት የሚያቀርባቸውን የምግብ ድጋፎች እንዲሰራጩ ብሎም ሌሎች ለጋሾች ተረጂዎች ወደሚገኙባቸው አካባቢዎች እንዲደርሱ የሚያስችሉ ተግባራትን አከውናለች ብሏል በመግለጫው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አባል ሃገራት አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታዎች የድርጅቱን መርሆዎች ባከበረ መልኩ ሰብአዊነትን፣ ገለልተኛነትን እና ነፃነትን በማስቀደም በተከታታይ እንዲደርሱ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ምክር ቤቱም በትግራይ የሰብአዊ እርዳታዎችን በቀጣይ የማድረስ ርምጃዎች ላይ እንቅፋት እንደሚፈጥር በመገንዘብ ክልሉ ወደ መደበኛ ሰላሙ እንዲመለስ ጠይቋል።

የምክር ቤቱ አባል ሃገራት በትግራይ ክልል የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ያደረሱ አካላትን በተገቢው ምርመራ ወደ ህግ እንዲቀርቡ ጠይቀው፤ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን እና የመንግስታቱ ድርጅት ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ያደረጓቸውን ጥረቶች በበጎ እንመለከተዋለን ብለዋል። በተመሳሳይ የአፍሪካ የሰብአዊ እና ህዝቦች መብቶች ኮሚሽን በዚህ ጉዳይ ላይ ያደረገውን ተሳትፎ በደስታ መቀበላቸውንም ተገልጿል።

በዚህም አለም አቀፍ ህግጋት ያለምንም መሸራረፍ መከበር እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል ተብሏል፡፡ምክርቤቱ አህጉራዊና ክፍለ አህጉራዊ ድርጅቶች ለሚያደርጋቸው ጥረቶች ያለውን ድጋፍ ገልጾ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በተለይ የሚያደርገው ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል ፡፡የፀጥታው ም/ቤት አባል ሃገራት ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ነፃነት፣ የግዛት አንድነት እና የዜጎች ህብረት ያላቸው አቋም ጠንካራ መሆኑን ማረጋገጡን በመግለጫው አስፍሯል።

(ኢዜአ)

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments