Sunday, October 13, 2024
Google search engine
HomeEthiopiaየሽብርተኛው ጁንታ ተፈላጊ ወንጀለኞች በአፋር ክልል ሾልከው የሚወጡበት ምንም አይነት ክፍተት አለመኖሩን...

የሽብርተኛው ጁንታ ተፈላጊ ወንጀለኞች በአፋር ክልል ሾልከው የሚወጡበት ምንም አይነት ክፍተት አለመኖሩን የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አረጋገጠ ።

የሽብርተኛው ጁንታ ተፈላጊ ወንጀለኞች በአፋር ክልል ሾልከው የሚወጡበት ምንም አይነት ክፍተት አለመኖሩን የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አረጋገጠ ።በሃገር ክህደት እና የሰሜን ዕዝ የሰራዊት አባላትን ከጀርባቸው በመውጋት ወንጀል የሚፈለጉት የህወሃት አመራሮችና ታጣቂዎች በአፋር ክልል ድንበር ሾልከው ለማምለጥ የሚችሉበት ምንም አይነት ክፍተት እንደሌለ የአፋር ክልል የፀጥታ ሃይል አመራሮች ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ኢብራሂም ሁመድ እንደተናገሩት ፣ የጁንታው ሃይል ከፈፀመው ሃገርን የማፍረስ ሙከራ በሗላ መንግስት የህግ ማስከበር እና የህልውና ዘመቻ ውስጥ ከገባበት እለት አንስቶ ፣ የአፋር ክልል የፀጥታ `ሃይሎች በተቀናጀ ሁኔታ ከመከላከያ ሰራዊታችን ጋር ተሰልፈው ለሃገራቸው ከፍተኛ መሰዋዕትነት በመክፈል ለተገኘው ድል የበኩላቸውን አስተዋኦ አብርክተዋል ።

አቶ ኢብራሁም ፣ ጁንታው ተደምስሶ ወደ ጫካ ከተበተነ በሗላ አመራሮቹና አጃቢዎቻቸው በአፋር በኩል ወደ ውጭ ለመውጣት የሚያደርጉት ጥረት በአፋር ክልል የፀጥታ ሃይሎች እና በክልሉ ህዝብ ጥረት መውጫ ቀዳዳ እንዳያገኙ ተደርጓል ብለዋል ።

በአሁኑ ወቅትም በአካባቢው ካለው የመከላከያ ሰራዊታችን ጋር በመተሳሰር ድንበሩ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ዝግ ስለተደረገ የጁንታው ወንጀለኞች ከኢትዮጵያ የሚወጡበት ምንም ቀዳዳ የለም ብለዋል፡፡የአፋር ክልል ሚሊሽያ ጉዳይ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አይዳሂስ አፍቅኤ በበኩላቸው ፣ የጁንታው የሃገር ክህደት ወንጀልን ተከትሎ በተወሰደው የህግ ማስከበር ግዳጅ እንዲሁም ሽብርተኞችን በማደንና በመልሶ ግንባታ ምዕራፎች ውስጥ የአፋር ክልል የፀጥታ ሃይሎች የተሰጣቸውን ግዳጅ መስዋዕትነት በመክፈልም ጭምር በብቃት ተወጥተዋል ብለዋል ።

ወንጀለኞች ከህግ ለማምለጥ የሚያደርጉት መፍጨርጨር በክልሉ የፀጥታ ሃይሎች ከፍተኛ ጥንቃቄ የከሸፈ ሲሆን ፣ ሽብርተኞቹ እስከሚያዙ አልያም እስኪደመሰሱ ድረስ ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር በመተሳሰር ድንበሩን የመዝጋት ተልዕኳችንን በታላቅ ሃላፊነት እንወጣለን ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡

ዳንኤል አወል

ፎቶግራፍ እታለም ሰበቦ

ምንጭ | የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments