ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን ተቋቁማ ሁለተኛውን ዙር የአባይ ግድብ ውሃ ከሞላች፣ ለ 90 ዓመታት ገደማ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ ጸንቶ የቆየው የሃይል አሰላለፍ መለወጥ ይጀምራል።
ኢትዮጵያ የራሷን ብቻ ሳይሆን፣ የአካባቢው አገራትን እጣ ፋንታ መወሰን በምትችልበት ቁመና ላይ ትሆናለች። ከአድዋ ድል በኋላ አውሮፓውያን አዲስ አበባ ላይ ቆንስላቸውን ለመክፈት ይሯሯጡ ነበር።
ኢትዮጵያን ለማየት የማይጓጓ አውሮፓዊና አሜሪካዊ አልነበረም። በአጼ ሚኒሊክ ስም ሳይቀር ጋዜጦች መታተም ጀምረው ነበር። የአድዋ ድል የኢትዮጵያን የአለማቀፍ ማህበረሰብ አባልነት ያረጋገጠ አስገራሚ ክስተት ነበር።
የአባይ ግድብም በተመሳሳይ ደረጃ የሚታይ ክስተት ይሆናል። ኢትዮጵያ በዙሪያዋ ላሉ ፕላኔቶች የምታበራ ጸሃይ ትሆናለች። ኒውክሊየር እንደታጠቀ አገር በአለማቀፍ መድረኮች ላይ “መንጎማለል” ትችላለች። ልብ በሉ ሁሉም ነገር በአንዴ ይለወጣል እያልኩ አይደለም። የእውነተኛ ለውጥ ጅማሮ እንደሚበሰር ግን በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ።ኢትዮጵያን የሚወድ፣ ከራሱ በላይ ለአገሩና ለመጪው ትውልድ የሚያስብ፣ ከቅናትና ከጥላቻ የጸዳ አዕምሮ ያለው ሁሉ ለአገሩ የሚቆምበት ጊዜ አሁን ነው። ለአገር መቆም ማለት ለአንድ ፓርቲ ወይም መንግስት መቆም ማለት አይደለም። ለአገር መቆም ማለት ለኢትዮጵያ ክብር መቆም ማለት ነው። ለኢትዮጵያ ዘላለማዊነትና ክብር በጋራ እንቁም!
Fasil Yenealem