Friday, April 19, 2024
Google search engine
HomeEducationበአማራ ክልል የዩኒቨሪሲቲ መግቢያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ተሸለሙ

በአማራ ክልል የዩኒቨሪሲቲ መግቢያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ተሸለሙ

በአማራ ክልል የዩኒቨሪሲቲ መግቢያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ተሸለሙየ2012 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው 600ና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ 156 ተማሪዎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ባለሀብቶች፣ ተማሪዎችና ወላጆች በተገኙበት ዛሬ በባህርዳር ከተማ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

አማራ ክልል ትምህርት ቢሮ 1.2 ሚለየን ብር፣ አቶ ካሳሁን ምስጋናው 1.5 ሚሊየንን ብር ፣ አቶ ወርቁ አይተነው 3 ሚሊየን ብርና የአማራ ክልል ዩኒቨሪሲቲዎች ፎረም 200ሽህ ብር ለተማሪዎች ሽልማት አበርክተዉላቸዋል፡፡

በሽልማት ስነ- ስርአቱ የተገኙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሐላፊ ይልቃል ከፋለ/ዶክተር/ በሀገር አቀፍ ደረጃ ክልሉን ግንባር ቀደም እንዲሆን ላደረጉ ተማሪዎችና መምህራን ምስጋና አቅርበዋል፡፡

እንቁ ተማሪዎቻችን በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ሆኖም ውጤታማ መሆን እንደሚቻል አሳይተውናል ያሉት ቢሮ ኃላፊው ለቀጣይ ተማሪዎችም አርአያ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡

በትምህርት ቤቶች በቂ ግብአት ሳይሟላላቸው በተማሪዎች፣ በመምህራንና በወላጆች ድጋፍ ውጤታማ የሆኑ ተማሪዎች ለመማር ማስተማር ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረላቸው ከዚህ በላይ ውጤት ማሰመዝገብ እንደሚችሉ ማሳያ በመሆኑ መንግስት፣አጋር አካላትና መላው ህብረተሰብ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የተጀመረውን ስራ እንዲጠናከር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው የክልላችን መውጫ በር እውቀት ነው ብለዋል፡፡ተሸላሚ ተማሪዎች የክልላችን ኩራት በመሆናቸዉ የክልሉ መንግስት ከጎናቸዉ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ተሸላሚ ተማሪዎች ክልሉ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ በሆነበትና ያልተሟላ የትምህርት ግብአት ባለበት ሁኔታ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርግ ውጤት ማስመዝገባችዉን አድንቀዉ ለዚህ ውጤት መሳካት ጉልህ ሚና ለነበራቸው መምህራን ምስጋና አቅርበዋል፡፡ተማሪዎች ወደ ዩኒቭርሲቲ ሲገቡ አዲስ የህይወት መንገድ የሚጀምሩበት ጊዜ በመሆኑ ለትምህራታቸው ብቻ ትኩረት በማድረግ የትምህርት ሰው ሊሆኑ እንደሚገባ መክረዋል፡፡ የክልሉን ትምህርት ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም አካል እንዲረባረብ ጥሪ ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ የሽልማት ስነ-ስርዓት የተሳተፉ አካላትን አመስግነዋል፡፡

SOURCE:Amhara Education Bureau

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments