Thursday, September 19, 2024
Google search engine
HomePoliticsሀገር አቀፍ የጸሎትና የምሕላ መርሀ-ግብር እየተካሄደ ነው

ሀገር አቀፍ የጸሎትና የምሕላ መርሀ-ግብር እየተካሄደ ነው

ሀገር አቀፍ የጸሎትና የምሕላ መርሀ-ግብር እየተካሄደ ነው

ሀገር አቀፍ የጸሎትና የምሕላ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሀ-ግብሩ ላይ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የየቤተእምነቶቹ አባቶችና የተለያዩ ታዳሚዎች የተገኙ ሲሆን በወቅታዊ ሀገራዊ ችግሮች ላይ ፀሎት እንደሚደረግም ተከልጿል።

የጸሎትና የምሕላ መርሀ-ግብሩ በአገሪቱ ያለው ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታ፣ ሰላምና መረጋጋት እጦትን፣ ብሔርን እና ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ ግጭትና ግድያ መበራከትን፣ ሃገራዊ ምርጫ ዝግጅትን፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተባብሶ መቀጠልን፣ የሃገራዊ ድንበር ውጥረትን እና መሰል ችግሮችን አስመልክቶ የሚደረግ ነው።

ኢትዮጵያውያን በሙሉ በዚህ አሳሳቢና አስጨናቂ ወቅት በጋራ በመሆን በፈጣሪ ፊት ንስሃ በማድረግ እና በእርቅ መንፈስ በአንድ ልብ ለጸሎት እንዲነሱ ዓላማ በማድረግ የታወጀ መርሀ-ግብር መሆኑን ነው የተገለፀው።

Source: EBC

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments