Thursday, September 19, 2024
Google search engine
HomeBAWZA NEWSታሪኩ ጋንኪስ /ዲሽታ ጊና/ ከመንግስትና ከአድናቂዎቹ ዳጎስ ያለ የገንዘብና የዓይነት ሽልማት ተበረከተለት

ታሪኩ ጋንኪስ /ዲሽታ ጊና/ ከመንግስትና ከአድናቂዎቹ ዳጎስ ያለ የገንዘብና የዓይነት ሽልማት ተበረከተለት

በደቡብ ኦሞ ዞን ለታሪኩ ጋንኪስ /ዲሽታ ጊና/ ከመንግስትና ከአድናቂዎቹ ዳጎስ ያለ የገንዘብና የዓይነት ሽልማት ተበረከተለትሀዋሳ፡ ግንቦት 18/2013 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር ለታሪኩ ጋንኪስ /ዲሽታ ጊና/ የ100 ሺህ ብር እንዲሁም ሁሉም ወረዳዎች ከ10 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር ሽልማት አበርክተዋል፡፡

አንድናቂዎችና ደጋፊዎች ደግሞ የዓይነትና የገንዘብ ሽልማት ሲሰጡ የደቡብ ኦሞ ህዝቦች ልማት ማህበርና የአሪ ህዝቦች ልማት ማህበርም የ8 እና የ30 ሺህ ብር ሽልማት አበርክተዋል።የጂንካ ከተማ አስተዳደር የ470 ካሬ ሜትር የመኖሪያ ቤት ግንባታ ቦታ ካርታ አስረክቧል።የናሳ እርሻ ልማት አግሮ ኢንዱስትሪ የግል ካምፓኒ ባለቤት አቶ ገበየሁ ምናሉ 40 ሺህ ብር ሸልመዋል።

ለታሪኩ ጋንኪስ /ዲሽታ ጊና/ የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደርን ጨምሮ የወረዳ አመራርና አድናቂዎች በጂንካ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በቦታው በመገኘት ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል።

ታሪኩ ጋንኪስ ወይም ድሽታ ጊና ሙዝቃ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከሀገር አልፎ ዓለም አቀፍ ዝናን አትርፎ ሙዝቃውን በርካቶች በመላው ዓለም እየተቀባበሉት ይገኛል።ታሪኩ ጋንኪስ ስራውን የሚያደንቁለት በተለያዩ ሚዲያዎችና ዝግጅቶች እንዲያቀርብ ጥሪ ባደረጉለት ግብዣ ከጂንካ ከአንድ ወር በላይ ወጥቶ ከቆየበት ሲመለስ ነው መላው የዞኑ ህዝብና አመራሮች እንዲሁም የሥራው አድናቂዎች በነቂስ ወጥቶ አቀባበል ያደረጉለት።

“የምድሯ ስራ እንጂ ዘር አያፀድቅም በእሱ ፊት፣ አዳም ወንድሜ ሄዋን እህቴ” ከግጥሙ ስንኞች መካከል መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያነቃነቀና በጎሳ፣ በዘር እንዲሁም በብሔርና በአካባቢ ከመታጠር በአንድ አዳም እና ሄዋን የሰው ዘር አንድ መሆኑን ያም አንድ ኢትዮጵያ የሚል መልዕክት አስተላልፏል፡፡ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከበደ ሳህለ በአቀባበሉ ወቅት እንደገለጹት በልዩነት ለታጠሩ አካላት ከታሪኩ ትክክለኛውን መረዳት ይችላሉ ብለዋል።

ሁላችንም አንድ ነን ያም ኢትዮጵያ የሚል አርማ ያለን ህዝቦች በመሆናችን ይህንን አንድነት በአለም አስመስክረናል በክፉም ሆነ በደጉ ብለዋል።የጂንካ ከተማ ከንቲባ አቶ ታዬ ጋንማይ በበኩላቸው ታሪኩ ጋንኪስ ለከተማውም ሆነ የዞኑ አምባሳደር በመሆኑ ትልቅ ክብር ይገባል ብሎ ሥራው ለሁሉም እንዲደርስ የጂንካ ከተማ አስተዳደር ድጋፉን እንደሚያደርግ ገልጸዋል።ዲሽታ ጊና ወይም ታሪኩ ጋንኪስ አድናቂዎቹና ለመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ስለተደረገለት ቅበላ አመስግኖ በህይወቱ በርካታ ውጣ ውረድ ማሳለፉንና አሁን ደግሞ እዚህ ደረጃ በመድረሴ ፈጣሪዬን እጅግ በጣም አመሰግናለሁ ብሏል።

ሁላችንም አንድ አባት እና አንድ እናት አለንና የአዳም ዘር በመሆኑ በመላው ሀገር ያሉ ህዝብ ይህ መልዕክት ይድረስ ብሏል የድሽታ ጊና ሙዝቃ ባለቤት ታሪኩ ጋንኪስ።የታሪኩ ባለቤት ወ/ሮ ራሔል ከነዶ ታሪኩ እንዲህ በአጭር ጊዜ ዕውቅና ማትረፉ ህልም እንደሚመስላት ገልፃ ለስራው ስኬት በጋራ ደፋ ቀና ሲሉ ወቆየታቸውን አስታውሳለች፡፡ ለዚህ ስኬት ያበቃቸውን ፈጣሪንም አመሰግናለች።የሀገር ሽማግሌዎችም አንድነት የሚሰብከው ሥራው ቀጣይነት እንዲኖረው አሳስበው መርቀዋል።

ዘጋቢ፡ ተመስገን አበራ – ከጂንካ ቅርንጫፍ

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments