Friday, December 13, 2024
Google search engine
HomeBAWZA NEWSየትንሳኤ በዓል ሲከበር ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በማሰብ እንዲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር...

የትንሳኤ በዓል ሲከበር ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በማሰብ እንዲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ

የትንሳኤ በዓል ሲከበር ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በማሰብ እንዲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጥሪ አቀረቡ

ህብረተሰቡ የትንሳኤ በዓልን ሲያከብር ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በማሰብ እንዲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ጥሪ አቅርበዋል።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን የ2013 ዓ.ም የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ ለክርስትና ዕምነት ተከታይ ወገኖች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ከመኖሪያ ቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች በዕለት ደራሽ እና በመልሶ ማቋቋም የድጋፍ አግባብ በፍጥነት ለመድረስ በሃላፊነት ስሜት ህብረተሰቡ እንዲረባረብም ነው አቶ ደመቀ መኮንን ያሳሰቡት።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በዚህ ጊዜ የሃገራችንን ልዑኣላዊነት አስጠብቆ ለማስቀጠል፤ የሰላም ዘብ ሆነን ለመዝለቅ እንዲሁም የተጋረጡብንን ፈተናዎች በድል ለመሻገር በፅናት ተደጋግፈን እና ተሳስበን በአንድነት የምንቆምበት ወሳኝ ወቅት ላይ እንገኛለን” ብለዋል።በተለይ በየአከባቢው በተከሰቱ ግጭቶች እና ማንነትን መሰረት በማድረግ በተፈፀሙ ጥቃቶች ምክንያት በርካታ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ በመሆኑ፤ ለነዚህ ወገኖች ትርጉም አዘል ድጋፍ እና ፈጣን ምላሽ መስጠት እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል።

መንግስት የዜጎችን ደህንነት የማስጠበቅ፤ የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ እንዲሁም በሁሉም አካባቢዎች ፀጥታና ሰላም የማስፈን ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።በዓሉ በሚፈጥረው መልካም አጋጣሚ ኢትዮጵያዊ መተሳሰብ እና መደጋገፍ የሚነግስበት እንዲሁም ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነታችን የሚጠብቅበት እንደሆን ተመኝተዋል።

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments