Tuesday, April 16, 2024
Google search engine
HomeSportsበቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሚሆነው ክለብ የ1ሚሊዮን ብር ተሸላሚ እንደሚሆን የፕሪሚየር...

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሚሆነው ክለብ የ1ሚሊዮን ብር ተሸላሚ እንደሚሆን የፕሪሚየር ሊጉ ሸር ካምፓኒ አስታውቋል

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሚሆነው ክለብ የ1ሚሊዮን ብር ተሸላሚ እንደሚሆን የፕሪሚየር ሊጉ ሸር ካምፓኒ አስታውቋል፡፡ ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 07/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የፕሪሚየር ሊጉ ሸር ካምፓኒ በ2013 ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሽልማትንና አጠቃላይ የውድድር ሂደትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

በ2013 የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ የሚሆነው ክለብም የ1 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ እንደሚሆን ታውቋል። ሁሉም ተሳታፊ ክለቦች እንደየደረጃቸው የሽልማቱ ተካፋይ ሲሆኑ ሁለተኛ ሆኖ ለሚያጠናቅቅ ክለብ የ700ሽህ እንዲሁም 3ኛ ሆኖ ለሚጨርስ የ500 ሽህ ብር ሽልማት ይሰጣቸዋል ብሏል ።

ፕሪሚየር ሊጉ ሳይጠናቀቅ አሸናፊው ከታወቀ ዋንጫው ለአሸናፊው ቀድሞ እንደሚሰጥም የፕሪሚየር ሊጉ ሸር ካምፓኒ የውድድር ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ገልፀዋል ። ቁመቱ 15 ሴንቲ ሜትር ክብደቱ ከ15 እስከ 20 ኪሎ ግራም የሚመዝን ደረጃውን የጠበቀ ዋንጫም ደቡብ አፍሪካ ውስጥ እየተሠራ እንደሆነና በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት እንደሚገባ ተገልጿል ።

ፕሪሚየር ሊጉ ግንቦት 18 ይጠናቀቃል። ግንቦት 21 ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ የኮኮቦች ሽልማት ይሰጣል። ለኮኮቦች የሚሰጠው ሽልማት እስካሁን ባይገለፅም ወጭውን ሱፐር ስፖርት ዲኤስ ቲቪ ይሸፍናል። የፕሪሚየር ሊጉ የመጨረሻ አምስት ሳምንታት ጨዋታዎች በሃዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም እንደሚካሄዱም ታውቋል። የ2014 ቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ምዝገባ ደግሞ ከሐምሌ 1 እስከ 15/2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት ይካሄዳል ።ሊጉንም መስከረም 7/2014 ዓ.ም ለመጀመር ታቅዷል። የተጫዋቾች ዝውውር ከሀምሌ 1 እስከ መስከረም 6 ባለው ጊዜ ይከናወናል።

ዘጋቢ፡- ባዘዘው መኮንን —ከአዲስ አበበ

Source: AMC

RELATED ARTICLES

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Google search engine

Most Popular

Recent Comments