ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲና ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በአፍሪካ የቮሊቦል ክለቦች ውድድር የመጀመሪያ ውጤት አስመዘገቡ
በአፍሪካ የሴቶች የቮሊቦል ክለቦች ውድድር እየጠሳፉ የሚገኙት ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲና ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በአፍሪካ የሴቶች የቮሊቦል ክለቦች ውድድር የመጀመሪያ ድላቸውን አስመዝግበዋል።
በ32ኛው የአፍሪካ የሴቶች የቮሊቦል ክለቦች ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ በምድብ ሁለት በመሳተፍ ላይ የሚገኘው ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በአራት የጨዋታ ክፍለ ጊዜ የቡርኪናፋሶውን ኤስ ዱዋኔስ 3 ለ 1 አሸንፏል።በምድብ አንድ የሚገኘው ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲና የቡሩንዲው ሙዚንጋ ጨዋታቻውን ማድረግ ነበረባቸው።
ይሁንና የሙዚንጋ ክለብ ተጫዋቾች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጋላጭነት ምክንያት ጨዋታውን ማድረግ እንደማይችሉ በመረጋገጡ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በፎርፌ ማሸነፉን ኮንፌዴሬሽኑ አስታውቋል።
የአፍሪካ ቮሊቦል ኮንፌዴሬሽን በፌስቡክ ገጹ ባሰፈረው መረጃ ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በመጀመሪያ ተሳትፎው የመጀመሪያ ድሉን በማስመገብ ኢትዮጵያን አኩርቷል ሲል ገልጿል።በቱኒዚያ በመካሄድ ላይ ያለው 32ኛው የአፍሪካ የሴቶች የቮሊቦል ክለቦች ውድድር ከሚያዚያ 13 ጀምሮ እስከ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ይቆያል ሲል ኤዜአ ዘግቧል።
በአፍሪካ የሴቶች የቮሊቦል ክለቦች ውድድር እየጠሳፉ የሚገኙት ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲና ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በአፍሪካ የሴቶች የቮሊቦል ክለቦች ውድድር የመጀመሪያ ድላቸውን አስመዝግበዋል።
በ32ኛው የአፍሪካ የሴቶች የቮሊቦል ክለቦች ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ በምድብ ሁለት በመሳተፍ ላይ የሚገኘው ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በአራት የጨዋታ ክፍለ ጊዜ የቡርኪናፋሶውን ኤስ ዱዋኔስ 3 ለ 1 አሸንፏል።
በምድብ አንድ የሚገኘው ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲና የቡሩንዲው ሙዚንጋ ጨዋታቻውን ማድረግ ነበረባቸው። ይሁንና የሙዚንጋ ክለብ ተጫዋቾች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጋላጭነት ምክንያት ጨዋታውን ማድረግ እንደማይችሉ በመረጋገጡ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በፎርፌ ማሸነፉን ኮንፌዴሬሽኑ አስታውቋል።የአፍሪካ ቮሊቦል ኮንፌዴሬሽን በፌስቡክ ገጹ ባሰፈረው መረጃ ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በመጀመሪያ ተሳትፎው የመጀመሪያ ድሉን በማስመገብ ኢትዮጵያን አኩርቷል ሲል ገልጿል።
በቱኒዚያ በመካሄድ ላይ ያለው 32ኛው የአፍሪካ የሴቶች የቮሊቦል ክለቦች ውድድር ከሚያዚያ 13 ጀምሮ እስከ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ይቆያል ሲል
ኤዜአ ዘግቧል።