ደሞ አንተን ምን አገኘህ?

0
314
ደሞ አንተን ምን አገኘህ?

ድሮ ድሮ ማን እንዳቀነቀነው ባላውቅም ስለ በቆሎ እንዲህ ተብሎ ተዘፍኖ ነበር ። “ማሽላዬን በላው ነጎዴ ፥ የሰው ነገር አትስማ ሆዴ ።” የሚገርመው እስከዛሬ ድረስ ግን ነጎዴ የሚለውን ትርጉም ብጠየቅ ምን እንደሆነ አላውቀውም ። ለማንኛው ዛሬ ከአንድ ጎደኛዬ ቤት ሒጀ በቆሎው ተገዝቶ ሊጠበስ ሲሸለቀቅ(ሲገለጥ) ከዚህ በፊት አይተነው የማናውቀው እንግዳ ነገር አገኝተን ተገረምን ።ጎበዝ ነገሩ ሁሉ ምን እየሆነ ነው።?ለካ እኛ ብቻ ሳይሆን በቆሎውም ታሟል ።ለመሆኑ ይህ ዘረ መሉ የተዳቀለ በቆሎ ያሳየው እንግዳ ነገር ምን ይሆን ?በዚህ በኩል የቀድሞው የዝንባቡዬን ሮበረት ሙጋቤንና የኬናያ እስካሁን ያሉት መሪዎችን አደንቃለሁ እስካሁን የኬንያ በቆሎ በተፈጥሮ የተገኘው እንጅ በማደቀል የተፈጥሮ በቆሎን አንቀይርም በማለት እንደፀኑ ናቸው ምንም እንኳ ከ2ዐዐዐ ዓ/ም አሜሪካ በካርተር አማካኝነት በሳሳካ ግሎባል አፍሪካን ምርታማ ለማድረግ የተሸረበው ሴራ ውጤት ሰለባም ሊሆን ይችላል ።ለማንኛውም የዘርፉ ባለሙያዎች እስቲ ሐሳብ ስጡበት ። የምንኖረው የማንኖረውን ዘመን ቢሆንም ያለፈው የሕይዎት ስንክሳራችን የአሁናችንን መኖር ብዙ ፈተና ገጥሞታልና የምሕረት እና የይቅርታ ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር ሆይ የሆነብንን ነገር ሁሉ ከእኛ አርቅልን።አሜን ለይኩን!

Teshome Achamyeleh