የመጀመሪያው ዙር እምቦጭ አረምን የመንቀል ዘመቻ ነገ ከጥዋቱ 12 ሰአት በሚደረግ ጉዞ ይጀመራል ።

0
254

ሁሉም ነገር ተጠናቋል ። የመጀመሪያው ዙር እምቦጭ አረምን የመንቀል ዘመቻ ነገ ከጥዋቱ 12 ሰአት በሚደረግ ጉዞ ይጀመራል ። ከማውራት በዘለለ የተግባር ስራ እየሰራን ለኢትዮጲያ አይን ለሆነው ለጣና ሀይቅ ሁሉም የበኩሉን በማድረግ ትግል የምናደርግበት ዘመን ሊሆን ይገባል፣የአንድ ሰሞን ጫጫታ ሆኖም መቅረት የለበትም ከተባበርን አንድ ወረዳ ለአንድ ሳምንት በሚል አንድ አመት ሙሉ ብንከት እመኑኝ እምቦጭ ታሪክ ይሆናል፣ጣናም መዳን ይጀምራል። ወደፊት ጥቂት እያወራን ብዙ እየሰራን ለጣና ፀረ የሆኑ አመራሮችንም አብረን እያረምን ታሪክ እንሰራለን ብየ አስባለሁ። በፍፁም ተስፍ አንቆርጥም። እግዚአብሄርም ይረዳናል። ተስፍ በአምላክ ነውና ተስፍ እናደርጋለን።ለዛሬው ነገ ከጥዋቱ 12 ሰአት ጣና ሀይቅ ት/ት ድርጂት እንገናኝ። ፌስ ማስክ መልበስ አይረሳ።ከጥዋት ሂደን ወደ ምሽት እንመለሳለን።ጉዞው እንዲሳካ ያደረጋቹህትን ከ 3 የማትበልጡ ግለሰቦችን ዘርዘር አድረገን በቀጣይ የምናመሰግን ይሆናል።

Metages Ethio

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here