የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

0
1054

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያየቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው በገንዘብ ሚኒስትር ተዘጋጅተው በቀረቡ የብድር ስምምነቶችና ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆች እና የኢሚግሬሽን፣ የዜግነትና የወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ስልጣን ተግባርና አደረጃጀት ለመወሰን በቀረበው ደንብ ላይ ነው ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በገንዘብ ሚኒስትር ተዘጋጅተው በቀረቡ የብድር ስምምነቶችና ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆች ላይ ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና ድጋፍ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ በኢፌዴሪ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል የተደረገ የብድር ስምምነት ላይ ተወይይቶ ውሳኔ ካሳለፈባችው ጉዳዮች መካከል ቀዳሚው ነው፡፡

በመቀጠልም ለሴቶች ንግድ ስራ ፈጠራ ብቃት ማሳደጊያ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ በኢፌዴሪና በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ መካከል የተደረገ የብድር ስምምነቶች ላይም ወሳኔ አሳልፏል፡፡

በኢፌዴሪና በጣልያን ሪፐብሊክ መንግስት መካከል የተደረገ 2 የብድር ስምምነቶች ከሀገሪቱ የብድር አስተዳደር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣሙ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ይጸድቁ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷቸዋል፡፡

ምክር ቤቱ ቀጥሎ የተወያየው የኢሚግሬሽን፣ የዜግነትና የወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ስልጣን ተግባርና አደረጃጀት ለመወሰን በቀረበው ደንብ ላይ ነው።

የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሰረት የኢሚግሬሽን ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ እና የብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎት አሰጣጥ ከስራ ባህሪ አንጻር በአንድ ኤጀንሲ እንዲደራጁ በመደረጉ የኢሚግሬሽን የዜግነት ኩነት ኤጀንሲ ስልጣን ተግባርና አደረጃጀት ለመወሰን የሚያስችል ረቂቅ ደንብ በሰላም ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አቅርቧል።

ይህንንም ተከትሎ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ማሻሻያዎችን በማከል ደንቡ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል።

/ጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት/