አና ጎሜዝ በኢትዮጵያ

0
801

 የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት አባልና የፖርቹጋል ተወላጇ አና ጎሜዝ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።

በምርጫ 97 የአውሮፓ ኅብረት ታዛቢ ልዑክ መሪ የነበሩት እና ጎሜዝ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ በርካታ ደጋፊዎቻቸው ተቀብለዋቸዋል።

አና ጎሜዝ በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ወቅት ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን ለውጥ አድንቀዋል።