ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ከቢል ጌትስ ጋር ተወያዩ

0
558

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ከቢል ጌትስ ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ቢሊየነሩን ቢል ጌትስ ዛሬ በጽህፍት ቤታቸው ተቀብለው በስዊዘርላንድ ዳቮስ የጀመሩትን ውይይት ቀጥለው ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባሳለፍነው ጥር ወር በስዊዘርላንድ ዳቮስ በነበራቸው ቆይታ የቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ተባባሪ ሊቀመንበር ከሆኑት ቢል ጌትስ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ይታወሳል።

በውይይታቸውም በግብርና፣ መስኖና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ለመተባበር መስማማታቸው ይታወሳል።

እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ በጤና፣ ግብርና እና አቅም ግንባታ ዘርፎች ለሚያደርገው ድጋፍ አመስግነዋል።
(ኤፍ.ቢ.ሲ)