አና ጎሜዝ ወደ ኢትዮጵያ

0
589

በምርጫ 97 የአውሮፓ ታዛቢ ልኡክ መሪ የነበሩት እና ጎሜዝ፤ የፊታችን አርብ  ለ3 ቀናት ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ሲሆን ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር እንደሚወያዩና በሚሌኒየም አዳራሽ ለህዝብ ንግግር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡  
የአውሮፓ ፓርላማ አባሏ አና ጎሜዝ፤ በሃገሪቱ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ተቋማት፣ ጋዜጠኞችና ታዋቂ ግለሰቦችም ጋር ተገናኝተው በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ይወያያሉ ተብሏል፡፡ የ97 ምርጫ ቀውስን ተከትሎ “ኢትዮጵያ ነፃ እስክትወጣ እታገላለሁ፤ከነፃነት በኋላ እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በአዲስ አበባ ጎዳና እንሸራሸራለሁ” ማለታቸው የሚነገርላቸው ጎሜዝ፤ “አሁን ያንን ቃሌን የምፈፅምበት ጊዜው ደርሷል” በማለት ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት እንደተዘጋጁ የአቀባበሉን ስነ ስርአት ያሰናዳው ኮሚቴ አስታውቋል፡፡  አዲስ አድማስ ጋዜጣ