በአማራ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው ልዑክ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በሰሜን አሜሪካ ያከሄደውን ጉብኝት አጠናቆ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ። 

0
825

በአማራ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው ልዑክ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በሰሜን አሜሪካ ያከሄደውን ጉብኝት አጠናቆ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ። 
የልዑካን ቡድኑ ከአማራ ተወላጆች እንዲሁም ከኢትዮጵያዊናንና ትውልደ ኢትዮጵያን ጋር በአምስት የተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ያደረገውን ውይይት አጠናቆ ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል።የቡድኑ አባላት ከዋሽንግተን ዳለስ አውሮፕላን ጣቢያ ሲነሱ ፕሬዝዳንት ገዱ አንዳርጋቸው ጉዟአቸው እጅግ የተሳካ እንደነበር ገልጸዋል። ከልኡካን ቡድኑ ጋር የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ/አዴፓ/ ስራአስፈጻሚና የጠቅላይ ሚንስትሩ የመሰረተ ልማት አማካሪ ዶር አምባቸው መኮንን እንዲሁም በምክትል መስተዳደር ማዕረግ የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ አቶ መላኩ አለበል አብረው ነበሩ።የአዴፓ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ምግባሩ ከበደም የዚሁ ጉብኝት አካል ነበሩ።

ተዋቸው ደርሶ ዋሽንግተን ዲሲ ዳላስ ኤርፓርት