የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ አዲሱ መፅሃፍ “ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር” በቅርቡ በሃገር ውስጥና በመላው አለም የሚሰራጭ ይሆናል።

0
1449
“ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር”
የአንዳርጋቸው ፅጌ አዲሱ መፅሃፍ

በወጣትነቱ ዘመኑ በተማሪዎች እንቅስቃሴና በኢሕአፓ አባልነት ጀምሮ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ትግል ውስጥ ከ40 አመታት በላይ ያልተቋረጠ ትግል እያደረገ ያለው የነፃነት አርበኛው አንዳርጋቸው ፅጌ በሕወሓት የማሰቃያ እስር ቤቶች ሆኖ የፃፈው መፅሃፉ ለአንባቢ ሊደርስ ነው።
“ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር” በሚል ርዕስ በቅርቡ ለገበያ የሚቀርበው የአንዲ መፅሃፍ ከኢሕአፓ ትግል እስከ ሕወሓት የመጨረሻዎቹ ዘመናት ድረስ የታዘበውን፣ የተመለከተውንና እርሱም የተሳተፈበት የትግል መንገድና የኢትዮጵያችን ሁናቴ በሰፊው ተቃኝቶበታል። 
አንዲ በማሰቃያ ቤት ላፕቶፕ እንዲሰጠው ጠይቆ ተሰጥቶት መፅሃፉን እዚያው ማሰቃያ ቤት መፃፍ የጀመረ ሲሆን ወደኋላ ላይ ግን በደኅንነቱ አጋፋሪ ጌታቸው አሰፋ ትዕዛዝ ላፕቶፑን እንዲቀማና በውስጡ የነበረውም የመፅሀፉ ረቂቅ አብሮ እንዲወረስ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም፤ በትረ ስልጣኑን ከአንባገነኖቹ ሕወሓታውያን የተረከበው የለውጡ ሃይል በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሳሳቢነት ላፕቶፑ እንዲመለስለት ማድረግ በመቻሉ አንዲ ኮምፒዩተሩን ለመረከብ በቅቷል።
“ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር” በቅርቡ በሃገር ውስጥና በመላው አለም የሚሰራጭ ይሆናል።

አቶ አንዳርጋቸውም ከዚያ ሁሉ መከራ ጠብቆና አውጥቶና የዘመናት ባለቤትና ሁሉን ማድረግ የሚቻለው ፈጣሪ እንኳን ለዚህ ታሪካዊ ጊዜ አደረሰህ።

 
Source: Petros Ashenafi Kebede