ህጻናትን ከስልክ እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ለማራቅ የሚያስገድዱ ሁኔታዎች

0
251

ህጻናት እንደ ላፕቶፕ፣ ታብሌት እና ስማርት ስልኮችን አዘውትረው የሚጠቀሙ ከሆነ ለተለያዩ የማህበራዊ እና የጤና ጉዳቶች ሊዳርጋቸው ይችላል።

ይህም ህጻናቱ ላይ በትምህርት፣ በማህበራዊ ግንኙነት እና የባህሪ ችግር በማስከተል ነው ይላሉ ተመራማሪዎች።

ከሚያደርሷቸው ጉዳቶች ውስጥም፦

1. የአእምሮ እድገት ላይ እክል ያስከትላል

ህጻናት ከተወለዱ ጊዜ አንስቶ እስከ 21 ዓመታቸው ድረስ አእምሯቸው እድገት በፍጥነት የሚያድግ ሲሆን፥ በዚህ የእድሜ ክልልውስጥ ያሉ ልጆች ጊዜያቸውን እንደ ላፕቶፕ፣ ታብሌት እና ስማርት ስልኮች የሚያሳልፉ ከሆነ አእምሯቸው ማደግ ፍጥነት ላይ እክል ሊገጥመው ይችላል።

2. ለሻከረ የማህበራዊ ግንኙነት ይዳርጋቸዋል

ጊዜያቸውን እንደ አይፓድ፣ ታብሌት እንዲሁም ስማርት ስልኮች ላይ የሚያሳልፉ ልጆች በማህበራዊም ይሁን በትምህርት ህይወታቸው ላይ ከፍተኛ ችግር ሲያጋጥማቸው ይስተዋላል።

just-one-more-tweet-dad.jpg

3. ከመጠን ላለፈ ውፍረት ይዳርጋቸዋል

ህጻናት ሙሉ ጊዜያቸውን እንደ ስማረት ስለኮች፣ አየፓዶች እና ኮምፒውተሮች ላይ ተቀምጠው የሚያሳልፉ ከሆነ ህጻናቱ የእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸው ዘገምተኛ ስለሚሆን ከመጠን ያለፈ ውፍረት /Obesity/ በቀላሉ ሊጋለጡም ይችላሉ።

የእንቅልፍ ማነስ፦ ህጻናት በሞባይል ስልኮት ላይ ባሉ መጫወቻ ጌሞች አብዛኛውን ጊዜ የሚጫወቱ ከሆነ ከእንቅልፍ ይልቅ ጨዋታውን ስለሚመርጡ በእንቅልፍ እጦት ምክንያት ለተለያዩ ችግሮም ሊጋለጡ ይችላሉ ተብሏል።

4. ለጨረር ይጋለጣሉ

141208144953-digital-life-image-3-be-a-champ-orig-ms-horizontal-large-gallery.jpg

ህጻናት የሞባይል ስልከም ይሁን ሌላ የኤሌከትሮኒክስ መገልገያ እቃዎችን አዘውትረው የሚጠቀሙ ከሆነ ቁሳቁሶቹ በሚያመነጩት ጨረር ለከፋ የጤና ችግር ሊያጋልጣቸውም ይችላል ተብልል።

5. አይንን ይጎዳል

e1c4988b385a338b2226fb044cdd8756_XL.jpg

ህጻናት በስከሪን ላይ እያዩ ለረጅም ሰዓት የሚቆዩ ከሆነ ለአይን ችግር ሊጋለጡ ይችላሉ።

ስለዚህም ህጻናት ሎጆችዎ የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች ላይ ረጅም ጊዜ የማሳለፍ ልምድ ካላቸው በአንድ ሰዓት ውስጥ ቢበዛ ለ30 ደቂቃ ብቻ እንዲጠቀሙ አድርጓቸው።

Source:- FBC