EPRDF Executive Committee concluded 18 days Meeting: FBC

0
1195

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባውን አጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባለፉት 18 ቀናት ሲያደርግ የነበረውን ስብሰባ አጠናቀቀ።

የሀገሪቱን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ ውሳኔዎች እንዳሳለፈ የሚጠበቀው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው፥ በስብሰባው ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች በተመለከተ ነገ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በስብሰባው ላይ ከአሁን በፊት ከተለያዩ የመንግስት የስራ ሀላፊነታቸው ለመነሳት ጥያቄ አቅርበው የነበሩት አቶ አባዱላ ገመዳ እና አቶ በረከት ስምዖን መንግስት እና ህዝብን እንዲያገለግሉ ወደተመደቡበት ቦታ ተመልሰው ለመስራት መስማማታቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያገኘው መረጃ ይጠቁማል።