English premier league: Best eleven players of the week

0
1079
best player of the week

#1. ግብ ጠባቂ – ማቲው ራያን (ብራይተን)

ማቲው ራያን ቡድኑ ብራይተን ከበርንሌይ ጋር በነበረው ፍልሚያ ስድስት ጎል ሊሆኑ የሚችሉ ኳሶችን አድኗል።

እንደ ብራይተን ላለ አደጋ ላይ ለሚገኝ ቡድን ጎሎች የሚያስፈልጉት ቢሆንም አንደ ማቲው ከሽንፈት የሚያድን ግብ ጠባቂ ደግሞ እጅግ አስፈላጊ ነው።

#2. ተከላካይ – ክሪስ ስሞሊንግ (ዩናይትድ)

ክሪስ ስሞሊንግ ለማንቸስተር ዩናይትድ ተሰልፎ ከተጫወተባቸው ጨዋታዎች መካከል ቡድኑ ዌስትብ ብሮምን ያሸነፈበት 99ኛው ድል ሲሆን ዩናይትድ በቀጣይ ሲያሸንፍ ስሞሊንግ 26ኛው 100 የድል ጨዋታዎች ላይ የተሰለፈ ‘ቀይ ሰይጣን’ ይሆናል።

አንቶኒዮ ቫሌንሲያ በጉዳት ሜዳውን ለቆ ሲወጣ የአምበልነት መለያውን ለስሞሊንግ አስረክቦ ነበር የወጣው። ቀጣዩ የቡድኑ አምበልነት ማዕረግ ወደየት እያመራ እንደሆነም ጠቋሚ ነው።

#3. ተከላካይ – ጄምስ ኮሊንስ (ዌስትሃም)

ዌስትሃም ስቶክ ሲቲን አሽንፎ ሶስት ነጥብ በሰበሰበበት ጨዋታ ኮሊንስ 18 ኳሶችን ከቡድኑ ግብ ክልል በማስወገድ ሚናውን ተጫውቷል።

በቅጣት ምክንያት ያልተሰለፈውን ዊንስተን ሬይድን ቀይሮ የገባው ኮሊንስ በጣም የሚገርም ብቃት ማሳየቱ ለዌስትሃም ድል ትልቁን ድርሻ እንደተወጣ እሙን ነው።

#4. ተከላካይ – ማርከስ አሎንሶ (ቼልሲ)

ማርከስ አሎንሶ የቼልሲን ማልያ ለብሶ በፕሪሚዬር ሊጉ መጫወት ከጀመረበት ሰዓት አንስቶ 10 ጎሎችን አስቆጥሮ አራት ደግሞ ለጎል የሚሆኑ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

አሁን ላይ ካሉ የፕሪሚዬር ሊጉ ተከላካዮች መካከል ማንም ይህንን ማሳካት አልቻለም።

ከሳውዝሃምፕተን ጋር በነበራቸው ጨዋታም እጅግ ድንቅ ጎል ማስቆጠርም ችሏል።

#5. አሮን ሙይ (ሃደርስፊልድ)

የሃደርስፊልዱ ሙይ በያዝነው የውድድር ዓመት አራት ኳሶችን ከመረብ በማገናኘት ከተላካይነት ሚናው ባለፈ ጎል አስቆጣሪነቱንም ተያይዞታል።

ከተከታታይ ሽንፈት በኋላም ቡድኑ ሃደርስፊልድ ዋትፎርድ በገዛ ሜዳው በመርታት ወደ አሸናፊነት መመለስ ችሏል።

#6. አማካይ – ኬቪን ደ ብሩይን (ሲቲ)

ደ ብሩይን ባለፉት 15 ጨዋታዎች ተሰልፎ ስድስት ጎሎች ሲያስቆጥር ስምንት ደግሞ አመቻችቶ በማቀበል ምን ያህል አስፈላጊ ተጫዋች እንደሆነ ማሳየት ችሏል።

ክሩክስ ደ ብሩይንን “የልጅ ፊት ያለው ገዳይ” ሲል ይጠራዋል።

#7. አማካይ – ፊሊፕ ኩቲንሆ (ሊቨርፑል)

ሊቨርፑል ከሜዳው ውጭ ተጫውቶ ካስቆጠራቸው ጎሎች ወስጥ ብራዚላዊው ኩቲንሆ ስምንት አስቆጥሮ ሰባት አመቻችቶ አቀብሏል።

ሊቨርፑሎች ኩቲንሆን በመያዛቸው ራሳቸውን ዕድለኛ አድረገው ሊቆጥሩ ይገባል።

#8. አማካይ – ሜሱት ኦዚል (አርሴናል)

ሜሱት ኦዚል ኒውካስትል ላይ ያስቆጠራት ጎል እጅግ ድንቅ ነበረች።

በኒውካስልና በአርሴናል መካከል የነበረው ትልቁ ልዩነት የሜሱት ኦዚል ጎል ነው። ምክንያቱም ኒውካስሎች ከጨዋታው ቢያንስ አንድ ነጥብ ለማግኘት በጣም ታግለው ነበር።

#9. አጥቂ – ዊልፍሬድ ዛሃ (ክሪስታል ፓላስ)

አሰልጣኝ ሮይ ሆጅሰን ክሪስታል ፓላስን ከተረከቡ ወዲህ የሚገርም ለውጥ ማምጣት ችለዋል፤ ቡደኑን ከወራጅ ቀጣና ከማውጣት ጀምሮ።

ሌይስተር ላይ ጎል ማስቆጠር የቻለው ዊልፍሬድ ዛሃ ደግሞ በዚህ ጉዞ ትልቅ ሚና ተጫውቷል።

#10. አጥቂ – ክሪስቲያን ቤንቴኬ (ክሪስታል ፓላስ)

ከ2012 ጀምሮ በተከናወኑ የፕሪሚዬር ሊግ ፍልሚያዎች ክሪስቲያን ቤንቴኬ 24 ጎሎችን በጭንቅላቱ ማስቆጠር ችሏል። በተመሳሳይ ጊዜ 27 የጭንቅላት ጎሎችን ካስቆጠረው የአርሴናሉ ጅሩድ ቀጥሎም ሁለተኛው ተጫዋች ነው።

የዛሃ፣ ቤንቴኬና ታውንሴንድ ጥሩ አቋም ላይ መገኘት ለፓላስ እጅግ መልካም ዜና ነው።

#11. አጥቂ – ራሂም ስተርሊንግ (ሲቲ)

በሁሉም ውድድሮች 15 ጎለችን ማስቆጠር የቻለው ስተርሊንግ የሲቲን ጎል ሰንጠረዥ እየመራ ይገኛል።

ሲቲ ከቶተንሃም ጋር በነበረው ጨዋታም ስተርሊንግ ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

BBC Amharic