አዳዲስ አስቂኝ የታክሲ ላይ ጥቅሶች!

0
3593

አዳዲስ አስቂኝ የታክሲ ላይ ጥቅሶች
1. እንኑር ብለን ነው እንጂ መሞት አያቅተንም!
2. የያዝናት እድሜ አይደለም ለጠብ ለፍቅር እንኩአን
አትበቃም!
3. ብቸኝነት ደስ የሚለው ሽንት ቤት ብቻ ነዉ
4. ማች ከመሞቱ በፊት ፍቅረኛውን ዜብራላይ ይስም ነበር
5. ጭቅጭቁን ትተን ብንፋቀር ምነው ሁሉም ቅርብ ወራጅ ነው
ከፈጣሪ በቀር
6. ታክሲ ዉስጥ መጨቃጨቅ ኣሸባሪነት ነው
7. ሰዉ ብቻ ነዉ የምንጭነዉ በስህትት የተሰቀለ ካለ ይዉረድ
8. የሰራ የእጁን የተቀመጠ የቂጡን ያገኛል
9. አንገትክ ብቆረጥም ዋናዉ ጤና ነዉ
10. መብትዎን ታክሲ ላይ ትዝ ኣይበልዎ
11. ጤፍና በርበሬ ሲወደድ ችላቹ ታክሲ ላይ ታማርራላቹ
12. መንግስትና ተሳፋሪ ሊወርዱ ሲሉ ነገር ነገር ይላቸዋል
13. ስልጣን የህዝብ ማስተዳደሪያ እንጂ ማስፈራሪያ አይደለም
14. የምተኛዉ የማይተኛ ጌታ ስላለኝ ነዉ
15. አምላኬ 100000000 ዶላር እና ጤንነቴን ስጠኝ
16. ጡትና መንግስት ጊዜውን ጠብቆ መውደቁ አይቀርም
17. ምከረው ምከረው አንቢ ካለ በሴት አስመክረው
18. ጎንበሥ ቀና ብዬ ባገለግላቸው ከወንዝ የተገኘ ድንጋይ
መሠልኳቸው
19. ፍቅረኛዬን አጣው ብለህ አትጨነቅ ታክሲም ማጣት አለና
20. ጠጋ ጠጋ በሉ! ! በኛ ታክሲ ተዋውቀው ብዙ ሰው ተጋብቷል
21. ነገረኛ ተሳፋሪ አደባባይ ላይ ” ወራጅ አለ ” ይላል
22. ሰውን ስትወድ ከመልካም ስብዕናው ውጪ ምኑንም ሳታይ
ይሁን
23. አንድ ማፍቀር ግድ ነው ሁለት ማፍቀር ግን ንግድ ነው
ሶስት ማፍቀር ግን ኮንትሮባንድ ነው
24. መዶሻ ጭንቅላት ያለው ሰው ሁሉም ስው ሚስማር
ይመስለዋል
25. ከሰራህ ትበላለህ ካልሰራ ሲበሉ ታያለህ
26. እግዝአብሄር ድሃን ማስደሰት ሲፈልግ አህያውን አጥፍቶ
እንዲያገኘው ያደርጋል
27. የበታችነት ከተሰማ ዛፍ ላይ ዉጣ
28. ጨበሶ ከመቃጠል በልቶ መመዘን ይሻላል
29. ቅናት ያገረጣዉ ፊት ቅባት አያወዛዉም
30. አስተዉሎ የሚራመድ ጫት ተራ ይደርሳል
31. እንኳን ተሳፋሪ ሙታንም ይሸጋሸጋል
32. ተሳፍሪ ጠጋጠጋ በሉ የአባይ አደራ አለብን
33. ባለጌ ሰው ዜብራ ላይ ወራጅ ይላል
34. ከጫት ሙቀት እንጂ አይገኝም እውቀት
35. ዜብራውን አንስተን አህያ እናስተኛልህ ወይ(ለሹፌሮች)
36. ለወሬኛ እና ለአምስት ሳንቲም መልስ የለንም
37. ፍቅር ፍቅር እያልሽ አትጨማለቂ ልቤ ዉስጥ ለመግባት
ጫማሽን አዉልቂ
38. አባይን ያላየ ሄዶ ማየት ይችላል
39. ሴት ልጅ ታርሳ የምትገኝ ቢሆን ኖሮ ወንድ ሁላ ገበሬ
ይሆን ነበር
40. ሰዉን አትናቁ ሰው እንዴት ይናቃል ቅማል እንኳን በአቅሙ
ሱሪ ያስወልቃል
41. እስቲ ይሁን ብለን የተከለዉ ቃጋ ጎበስ ጎበስ አለ እኛኑ
ሊወጋ
42. ባላገር ሲሰለጥን በዜና ይደንሳል
43. መሀይም ሀብታም ደሃን የፈጠረ ይመስለዋል
44. ምን ጊዜው ቢረዝምም ቋንጣ እና ባለ ስልጣን መውረዱ
አይቀርም
45. ዝናብ ጥሎ ጥሎ መሬቱ ጭቃ ሲሆን ያን እያነሱ
ግርግዳዉ ላይ ልጥፍ
46. በፍየል ዘመን በግ አትሁን
47. ሹፌሩን በፍቅር ማሣቅ እንጅ በነገር ማሣቀቅ ክልክል ነው
48. ትሞህርት በዱላ ቢሆን ኖሮ አህያ ፕሮፌሰር ትሆን ነበር
49. ሴት ልጅ ሒሣብ ሥትማር እንጂ ስትከፍል አይተን አናቅም
50. ደሀ ነዉ ችስታ ነዉ ብለሽ ትይኛለሽ ጭንና ዳሌ እንጂ
አንችስ ምን አለሽ
51. መልስ ለረሳ ማትሪክ ላይ እንመልሳለን
52. ሴትና ሎተሪ ለማይፈልጋቸዉ እንጂ ለሚፈልጋቸዉ
አይወጡም
53. ሹፌር ለጠበሰ ባለ 100ብር ረዳት ለጠበሰ ባለ 50
ብርካርድ እንሞላለን
54. የቅድብ ፀጉርና ምቀኛ አያድጉም
55. ንፁህ ህሊና ምቹ ትራስ ነዉ