በሊቢያ እየተካሄደ ያለውን የባሪያ ንግድ በመቃወም በናይጀሪያ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ

0
1221

ሊቢያ በጥቁር አፍሪካውያን ላይ እየፈጸመችው ያለውን የባርያ ንግድ በመቃወም በናይጀሪያ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡

በናይጀሪያ በተባበሩት መንግስታት አዳራሽ ፊት ለፊት በተካሄደው ሰልፍ የተገኘው የሰልፈኞች ቁጥር ቢያንስም ዓላማው ማስተማር ነው ሲሉ የፓን አፍሪካ ተሀድሶ ንቅናቄ አባል የሆኑት አይንክ አደፌሜ ለቢቢሲ ተናረዋል፡፡

የአፍሪካን ገጽታ የማይገልጽ ድርጊት ሊብያ ላይ እየተከናወነ መሆኑን ለማህበራዊ ሚዲያው አሳውቀናል፡፡

በአፍሪካ መንግስታት እና በተባበሩት መንግስታት ላይ ጫና ለመፍጠር የተካሄደ ሰልፍ ነው፡፡በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል፡፡

ምንጭ:- አብመድ