የስነ-ጽሑፍ ቅርሶች

0
3182

ባለፊደል ቋንቋን የታደለችው ኢትዮጲያ፣በስነ-ጽሑፍ ሀብቷም ትታወቃለች፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሳይንስ፣የትምህርት እና የባህል ዘርፍ የሆነውዮኔስኮ ከኢትዮጵያ 12 የሚደርሱ የስነ-ጽሑፍ ሀብቶችን የዓለም ቅርስ አድርጎ መዝግቧል፡፡መፅሀፈ ታሪከ ነገስት፣ፍትሃ ነገስት፣መፅሀፈ ሄኖክ፣የአፄ ቴዎድሮስ እና የአፄ ምኒሊክ ወደ እንግሊዝና ሩሲያ የተላኩ ደብዳቤዎች ወ.ዘ.ተ በዮኔስኮ ተመዝግበዋል፡፡

ጥንታዊ የብራና ስነ-ጽሑፍን ከስልጣኔዋ ጋር አዋህዳ የተጓዘችው ኢትዮጲያ ፊደሏም ቴክኖሎጂን እየተላመደ መጥቷል፡፡
በተለይም ዶክተር አበራ ሞላ ፊደላትን በ 1982 ዓ/ም ከኮምፒውተር ጋር ካላመዱ በኋላ ከእጅ ስልክ እስከ ጎግል መተርጎሚያ ድረስ ቋንቋችን ቴክኖሎጂን ተላምዷል፡፡
ከ 35 ዓመታት በላይ ኑሯቸውን በአሜሪካ ያደረጉት ዶክተር አበራ ሞላ፣በኢትዮጲያ ፊደል የኮምፒውተር አደራደር ከአሜሪካ የፈጠራ ባለቤትነት መብት አግኝተውበታል፡፡የፈጠራ ባለቤትነት መብቱን የኢትዮጵያ መንግስት እንዲሰጣቸው እየወተወቱ እንደሆነም በአንድ ወቅት ለዝግጅት ክፍላችን ተናግረዋል፡፡

ከፊደል እና ከቋንቋ በተጨማሪ የራሳችን የዘመን ቀመርም ከዓለም ይለየናል፡፡በጉዳዮ ዙሪያ ሰፊ ጥናት ያቀረቡት ዶክተር አበራ ሞላ የኢትዮጵያ የዘመን ቀመር ከሮማውያኑ የጎርጎርስ ቀመር ይለያል፡፡ትክክለኛው የኢትዮጵያ የዘመን ስሌት ነውም ይላሉ፡፡
ሀሳባቸውን ለቫቲካን ቤተክርስቲያን አቅርበው ተቀባይነት አግኝተዋል ፡፡
የእንግሊዙ ቴሌግራፍ እንዳስነበበውም፣የአውሮፓ የዘመን ቀመር እንደገና መጠናት እንዳለበት የቫቲካን ቤተክርስቲያን ዋቢ አድርጎ ጠቅሷል፡፡የቫቲካን ጳጳሳትም የአውሮፓ የዘመን ቀመር መቀየር እንዳለበት በመፅሃፋቸው ገልፀዋል፡፡http://www.ethiomedia.com/assert/4848.html

ባህረ ሀሳብን የመረመሩት ፕሮፊሰር ጌታቸው ሃይሌም፣የዘመን ቀመራችንን ምክንያታዊነት እና ሳይንሳዊነት አረጋግጠዋል፡፡
ይህ ሁሉ ሀሳብ የተገኘው በግዕዝ ከተፃፉ ሰነዶች ነው፡፡በመሆኑም ግዕዝን መመርመር ከትናንት ተነስቶ ወደ ነገ ለመሻገር መንደርደሪያ ሆኖ ያገለግላል ይላሉ ዶክተር አበራ ሞላ፡፡
ዶክተሩ እንደሚሉት በተለይም ስራዓተ ፅህፈቱን ለማሻሻል ያበለፀጉትን አዲስ ሶፍት ዌር መጠቀም ነገን ለመቅደም አስቻይ ሁኔታን ይፈጥራል ይላሉ፡፡

የባህር ዳር ዮኒቨርስቲም፣ ግዕዝን እና ጥንታዊት የኢትዮጵያ ታሪክን መመርመር የሚያስችል የትምህርት ክፍል ከፍቶ ከወራት በኋላ ማስተማር ይጀምራል፡፡የዚህ መርሃግብር አስተባባሪ ዶክተር ዳዊት አሞኘ የጥንታዊት ኢትዮጲያን(classical history of Ethiopia) ታሪክ ከግዕዝ ሰነዶች በመፈተሽ የሀገሪቱን ትክክለኛ የታሪክ ፣የፍልስፍና እና የልዮ ልዮ ሀገረሰባዊ ሀብቶችን ለማጥናት ታሳቢ ተደርጓል፡፡መርሃግብሩም በሁለተኛ ዲግሪ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
ባህርዳር ዮኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልፀጊያ ተቋም ከፍቶ የቋንቋውን የስነ-ጽሑፍ ሀብት ለማሳደግም እየሰራ ነው፡፡

ምንጭ:- ካነበብነው