Fassil Kenema plays against St. George!

0
856

ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ
•••••••••••••••••••••••••••••••••
በኢትዮጵያ ውስጥ በትልቅነቱ፣ በታሪካዊ መስህብነቱ እና የበርካታ ቱሪስቶችን ቀልብ የሚስበው ታላቁ የጣና ሀይቅ በእንቦጭ አረም ወረርሽኝ ህልውናው በከፍተኛ አደጋ ላይ መውደቁ የአደባባይ ሀቅ ነዉ፡፡ ይህንንም ታሳቢ በማድረግ የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብና የአምናው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን በባህር ዳር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ መስከረም 21 2010 ቀጠሮ መያዛቸው ይታዎሳል፡፡
ጨዋታው እንቦጭ አረምን ለማጥፋት የሚደረገው ዘመቻ አንዱ አካል ሲሆን በመጭው እሁድ የሁለቱ ቡድን ደጋፊዎችና ተጫዋቾች በተገኙበት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሁለገብ ስታዲየም ይደረጋል፡፡
በደቡብ ሪጅናል ካስትል ዋንጫ እየተሳተፉ የሚገኙት አፄዎቹ ዛሬ ሀሙስ ወደ ባህርዳር ሊያደርጉት የነበረዉ ጉዞ በበረራ ትኬት ማጣት ምክንያት ወደ ቅዳሜ ተዘዋውሮ የአፄዎቹ የቡድን ስብስብ ከጨዋታው አንድ ቀን ቀደም ብለዉ ወደ ክልላችን ርዕሰ መዲና ባህር ዳር ያቀናሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በደቡብ ሲቲ ካፕ ለግማሽ ፋፃሜ የደረሱት ፋሲሎች በነገዉ እለት ከአርባምንጭ ከተማ ጋር የሚጫወቱ ሲሆን ይህንን ጨዋታ ድል አድርገዉ ለፍፃሜ የሚደርሱ ከሆነ በዉድድሩ መጀመሪያ ከአዘጋጁ አካል ጋር በተደረገ ስምምነት የፍፃሜ ጨዋታዉ የተወሰኑ ቀናቶች እንዲራዘም ይደረጋል፡፡