Bee Farm-General knowledge

0
3520

ንብ እርባታ የንብ እርባታ በአብዛኛው አርሶ አደር በተጓዳኝ የሚካሄድ የግብርና ንዑስ የሥራ መስክ ነው። ልማቱ የሚካሄደው ማርና ሰም ለመሰብሰብና ለመጠቀም ሲባል ነው። ማር ለመድሃኒትነት የሚውል ሲሆን ከሰሙ ተሸጦ ለገቢ ምንጭ ማዳበሪያነት ያገለግላል። ማርና ሰምን ለዓለም ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ ያስገኛሉ። ንቦች ማርና ሰም በማምረት በሚያደርጉት ጥረት ከእፅዋት ፈሳሽ፣ የአበባ ወለላ (ኔክታር) እና የፅጌ ብናኝ (ፖለን) እፅዋቶች እንዲራቡ ያደርጋል።

በሃገራችን ብዙ የማር እፅዋት፣ አውራ ንቦች፣ በቂ ውሃና ለልማቱ መዳበር የሚስማማ የአየር ንብረትና የተፈጥሮ ቅንብሮች ይገኙበታል። በሀገራችን ከ10 ሚሊዮን በላይ አውራ ንቦች ይገኛሉ። 75% በባህላዊ፣በሽግግርና በባለፍሬም ቀፎ የሚራቡ ናቸው። በዓመት 28.5 ሺህ ቶን ያልተጣራ ማርና 3.2 ሺህ ቶን ሰም ይመረታል። ምርቱም ሀገሪቷ ካላት የተፈጥሮ ሀብት ጋር ሲነፃፀር በጣም አነስተኛ ነው።

ለዚህም ምክንያቶች፡-

• ባህላዊ መንገድ መሆኑ • በማናብ በቂ እውቀትና ክህሎት አለመኖር

• የግብርና ዘዴ በበቂ ሁኔታ አለመስፋፋት

• የማናቢያ መሣሪያዎች እጥረትና ውድነት

• የምርምር ተቋማት ውስንነት • የገበያና የብድር ሥርዓት አለመዘርጋት ናቸው። የንብ ቀፎ አይነቶች የላን ግስትሮዝ (Langstroth) የንብ ቀፎ ይህ የንብ ቀፎ የተንቀሳቃሽ ፍሬም አይነት ሲሆን ብዙ ተጠቃሚዎች አሉት፡፡ ፍሬሞቹ እርስ በርሳቸዉና ከቀፎዉ ግድግዳ ጋር በአንድ ንብ ርዝመት የተለዩ ናቸዉ፡፡ የላንግስትሮዝ ቀፎ በሳጥኑ ዉስት እስከ አስር ፍሬሞችን ይይዛል፡፡ አንዳንዴም ከ8 እስከ 12 ሊይዝ ይችላል፡፡ በምስሉ ላይ የሚታየዉ ባለ 10 ፍሬም ሁለት ፎቅ የላንግስትሮዝ ቀፎ ነዉ፡፡ በምስሉ እነደሚታየዉ ከላይ ወደታች የቀፎቹ አካላት ናቸዉ፦

• የላይ መሸፈኛ ወይም ጣሪያ

• የዉስጥ መሸፈኛ

• ሱፐር ወይም የማር ማስቀመጫ • የእጭ/እንቁላል ማስቀመጫ •

የታችኛዉ ሰሌዳ/ጣዉላ

• ማስተካከያ ሰሌዳ ወይም በቆሚያ ቶፕ ባር (Top-Bar) ቀፎ ይህ ቀፎ በአነስተኛ ወጪ የሚሰራ ሲሆን የላንግስትሮዝ ቀፎ አማራጭ ሆኖ ያገለግላል፡፡ አሰራራቸዉ ቀላል መሆኑና ርካሽ መሆናቸዉ ተመራጭ ያደርጋቸዋል፡፡ ይህ የንብ ቀፎ ተንቀሳቃሽ ፍሬም ያለዉ ነዉ፡፡ ንቦቹ የሚሰሩት እንጀራ ከላይ እንዲንጠለጠል ሆኖ ነዉ፡፡ ንቦቹ ማሩ ከተሰበሰበ በሗላ እንደገና እንጀራ መስራት ይኖርባቸዋል፡፡ይህ የንብ ቀፎ የማር ምርቱ አነስተኛ ሲሆን ሰም ግን ብዙ ይገኝበታል፡፡ የንብ እርባታ ዉጤቶች የሚክተሉት የንብ እርባታ ዉጤቶች ናቸዉ፦

• ማር፦ ለምግብነት ይዉላል፤ ለሌሎች ምግቦች እንደግብአት ያገለግላል፤ ለመድሐኒትነት ያገለግላል፤ የትንባሆን መዓዛ ለመጠበቅ ያገለግላል፤ ለኮስሜቲክስ፤ ለማለስለሻ፣ ለሳሙናና ለሻምፑ፤ እንዲሁም ለሊፕስቲክ መስሪያነት ያገለግላል፡፡

• ፖለን፦ ለምግብነት ከመዋሉም በላይ ለመድሃኒትና ለኮስሜቲክስ ያገለግላል

• ሰም፦ ለሻማ መስሪያ፤ ለኮስሜቲክስ፤ ለምግብ ማምረቻ፤ ለጨርቃጨርቅ፤ ለቫርኒሽና ፖሊሽ፤ ለህክምናና ቅረፃቅርፅ ለመስሪያ ያገለግላል፡፡

• ፕሮፖሊስ፦ የሚገኘዉ ከሰምና ንቦጩ ከሚሰበስቡት የተለያዩ አበቦችና ቅጠሎች ቅልቀል ነዉ፡፡ ለኮስሜቲክስ፣ ለህክምናና ለምግብ ኢንዱስትሪ ያገለግላል፡፡

• ሮያል ጄሊ፦ ይህን የሚያመነጩት በጣት ሰራተኛ ንቦች ሲሆኑ ንግስቲቷንና እንቁላሎችን ለመመገብ ያገለግላል፡፡ ሮያል ጄሊ ለእንስሳት መኖነት፣ ለኮስሜቲክስ እና እንደተጨማሪ ምግብ/dietary supplement ያገለግላል፡፡

• የንብ መርዝ፦ ንቦች በሚናደፉበት ወቅት እንደመከላከያ መረዝ ያመነቻሉ፡፡ ይህ መርዝ በንብ ንድፊያ ቢዜ የሚከሰትን አለርጂ ለመከላከል ይረዳል፡፡ የንብ እርባታንና ሌሎች የግብርና አይነቶችን ማቀናጀት የንብ እርባታ ከሌሎች የግብርና አይነቶች ገር በቀላሉ መቀናጀት ይችላል፡፡ ንቦች ሰብሎችን በማዳቀል አስተዋፀኦ ሲያደርጉ የተተከሉት ሰብሎች ደግሞ ለንቦቹ ማር መስሪያ ምግብ ይሆናሉ፡፡ የሚከተሉት ዕፅዋት በንቦች አማካኝነት በመዳቀል ከፍተኛ እርዳታ ያገኛሉ፦ ቃጫ፣ ሻይ፣ ፓፓያ፣ ኮኮነት፣ ቡና፣ ስኳሽ፣ ዱባ፣ ኩከምበር፣ ኮምጣጤ፣ አፕል፣ አቮካዶ፣ ሃብሃብ፣ ፒች፣ ሰሊጥ፣ ሱፍ እና የተወሰኑ የአኩሪ አተር ዝርያዎች ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ ደኖችም ለንቦች ግብአት ሲሆኑ ንቦችም እንዲሁም ለደን ጥበቃ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡ የንብ ጎጆና የንብ ቀፎዎች የንብ ጎጆ ማለት ትይዩ የሆኑ ተከታታይ ባለስድስት ጎን ቅርፅ ያላቸዉ ክፍልፋዮች ሲሆኑ ማር፣ ፖለን እና ላርቬ/እንቁላል ለማስቀመጥ ንቦቹ ይጠቀሙበታል፡፡ እነዚህ ረቀቅ ያሉ ቅርፆች ንቦቹ ትንሽ ንቦችን ለመንከባከብ፣ ማር ለማስቀመጥና ንግስቲቷን ለመጠበቅ ይጠቀሙበታል፡፡ የንብ ቀፎ ደግሞ ንቦቹ ጎጇቸዉን የሚቀልሱበት ቤት ነዉ፡፡ የንብ ቀፎዎች በሶስት ይከፈላሉ፡፡

እነዚህም፦ • ባሕላዊ ቀፎዎች፦ እነዚህ የሚሰሩት በአካባቢዉ በሚገኙ እንደ ሸምበቆ እና ሸክላ በመሳሰሉት የሚሰራ ነዉ፡፡ ማርና ሰም በሚሰበሰብበት ወቅት ብዙዎቹ ንቦች ሊሞቱ ይችላሉ፡፡

• ባለተንቀሳቃሽ ፍሬም ቀፎዎች፦ በጣም ዘመናዊ ሲሆኑ ከፍተኛ ምርትን ለመሰብሰብና ንቦቹንም ላለመረበሽ አይነተኛ ተመራጭ ነዉ፡፡ ብዙ ንቦችንም ማስተናገድ ይችላል፡፡ በአበባ ወቅቶችም ብዙ ማር ማስቀመጥ ይችላል፡፡

• ባለዝቅተኛ ቴክኖሎጂ ቀፎዎች፦ እነዚህ ቀፎዎች የባለተንቀሳቃሽ ፍሬምን ቀልጣፋነትንና ለአያያዝ ምቹነትን እንዲሁም የባሕላዊ ቀፎን ዝቅተኛ ዋጋ ያጣመሩ ናቸዉ፡፡ ንቦቹ ማሩን በተዘጋጁላቸዉ መደርደሪያዎች ላይ ያዘጋጃሉ፡፡ ይህ ቀፎ በአካባቢዉ ካሉ ቁሳቁሶች ሊሰራ ይችላል፡፡

ምንጭ ካነበብነው