ባውዛ ጋዜጣ ዝግጅት የኢ ኤስ ኤፍ ኤን ኤ ከኢትዮጵያ የስፖርት ፌዴሬሽን በኖርዝ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ጋር ከጁላይ 2-ጁላይ 8 2017 በሲያትል ስለሚደረገው ስፓርትና የባህል ዝግጅት እንዲያጫውቱን አጭር ቆታ አድርገን ነበር፤፤

0
2017
Getachew Tesfay ESFNA Prisedent

ባውዛ ጋዜጣ ዝግጅት የኢ ኤስ  ኤፍ ኤን ኤ ከኢትዮጵያ የስፖርት ፌዴሬሽን በኖርዝ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ጋር ከጁላይ 2-ጁላይ 8 2017 በሲያትል ስለሚደረገው ስፓርትና የባህል ዝግጅት እንዲያጫውቱን አጭር ቆታ አድርገን ነበር፤፤


 

Getachew Tesfay ESFNA Prisedent

 

ባውዛ፡- እስቲ ራሰዎን ያስተዋውቁ!

ስሜ ጌታቸው ተስፋዮ ይባላል፡፡ የኢ ኤስ  ኤፍ ኤን ኤ በኢትዮጵያ የስፖርት ፌዴሬሽን በኖርዝ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ለስድሥት ዓመታት በኃላፊነት አስተዳድሪያለሁ፡፡ ይሔ እንግዲህ የመጨረሻዮ ነው፡፡ አንድ ፕሬዚዳንት ማገልገል የሚችለው፡፡ ለስድሥት ዓመት ነው፡፡ ይሄም ማለት ሁለት ተርሞች ነው፡፡ ሦስት ሦስት ዓመት ሁለት ጊዜ፡፡

ባውዛ፡- የ2017 የኢ ኤስ  ኤፍ ኤን ኤ የት ነው የሚካሄደው?

አቶ ጌታቸው ፡- 34ኛ ዓመታችን ነው፡፡ የዘንድሮው ሲያትል ከተማ ውስጥ ነው፡፡ ይሄም በ34ኛ ዓመት ታሪካችን ሲያትል ወደ ሲያትል ምንሄደው ከ13 ዓመታት በኋላ ነው፡፡ በአአአ በ2004 ነበረ ሲያትል ጨዋታ የተደረገው፡፡ ሲያትል በጣም ቆንጆ ሀገር ነው፡፡ ሲያትል ሁልጊዜ ይዘንባል ይባላል፤ ነገር ግን ጁላይ ላይ ጥሩ አየር ነው ያለው፡፡ የወቅቱን መድረስ በደስታና በጉጉት እየጠበቅን ነው፡፡

ባውዛ፡- ከዓለም ላይ የሚመጡ ተሳታፊዎችንና የተመልካቾችን ለመቀበል መስተንግዶ ዝግጅትስ እንዴት ነው?

አቶ ጌታቸው ፡- በመጀመሪያ እንደውም አንድ ከተማ ለመሄድ ስንሰናዳ የስቴዲየሙን ሁኔታና አጠቃላይ የሆቴልና የማረፊያ ሁኔታዎችን ጉዳይችን እናጠናለን፡፡ ይሄንም በማደረግ ነው የዘንድሮውንም ወደ ሲያትል ከመሄዳችን በፊት ዝግጅታችንን የጨረስነው፡፡ ስቴዲዩሙ ሬንተን ሜሞሪያል ስቴድየም ይባላል በቅርብ ጊዜ የታደሰ ስቴድየም ነው፣ ከ6 እስከ 7 ሚሊዮን ዶላር አውጠተው ነው ያደሱት፡፡ መካከለኛና መለስተኛ በእኛ ልክ የተሰራ ነው የሚመስል፡፡  ለምንፈለጋቸው የመስተንግዶ፣ ለሸቀጣ ሸቀጦች መሸጫና አጠቃላይ ዝግጅቶቻችን በቂ አመቺ ሥፍራ ነው፡፡ የመኪና ማቋሚያም ያለው፣ በጣም ቆንጆ ነው ሰው ይወደዋል፡፡ ሆቴሎችም እዛው አካባቢ ናቸው፡፡ የያዝናቸው ሆቴሎች ሁለት ናቸው ፡፡ እኛ የያዝናቸው ሆቴሎች ተሽጠው አልቀዋል፡፡ ሦስተኛ ሆቴልም ልንጨምር ነው፡፡ ሰው በጉጉት ነው እየጠበቀ ያለው፡፡

ባውዛ፡- ምን ያህል ሰው ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል?

አቶ ጌታቸው ፡- በርግጥ ሲያትል ከተማው የኢትዮጵያዊው ብዛት እንደ ዋሺንግተን ወይንም እንደ ቶሮንቶ አይሆንም፡፡ ነገር ግን በአካባቢው ሌሎች ከተሞች ስላሉ ያንን ተስፋ እናደርጋለን አሁን ያለውን ሁኔታም ስናየው በርካታ ሰው ይመጣል ብለን እናስባለን፡፡ ከ13 ዓመት በፊት ስናዘጋጅ የአሁኑን ያህል ሰው አልነበረም፡፡ ግን በጣም ብዙ ሰው ገብቶ ነበር፡፡ በተለይም የ“ኢትዮጵያ ቀን” ተብሎ በሚጠራው ዝግጅት በርካታ ሰው ገብቶ ነበር፡፡ ልክ የዋሺንግተን ያክል ያክል ነው ሰው ገብቶ የነበረው፡፡ ሰው ሲያትል መሄድ ይወዳል፡፡ ምክንያቱም አየሩ አይሞቅም፡፡ በዚህ ወቅት በጣም ጥሩ ነው፡፡ ጠቅለል ስናደርገው በርካታ ሰው አንደሚመጣ ይጠበቃል፡፡ ስቴድየሙ መካከለኛና በቂ ነው፡፡

ባውዛ፡- በዘንድሮ ውድድር ምን ያህል ቡድኖች እንደሚሳተፉ ይታወቃል?

አቶ ጌታቸው ፡- ከዩናይትድ ስቴትስና ከካናዳ የሚመጡ ቡድኖች ናቸው የሚሳተፉት፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ሃያ ዘጠኝ ፤ ካናዳ ሁለት ክለቦች አሉ፡፡ እነዚህ ሠላሳ አንድ ክለቦች ናቸው በወንዶች ዲቪዥን የሚካፈሉት፡፡ በሴቶችም ዲቪዥን አለን፡፡ ከዋሺንግተን አንድ ቋሚ ክለብ አለን፤ እነርሱም ተካተው ሠላሳ ሁለተኛ ቡድን ናቸው፡፡ በሄድንበት ከተማ ሌሎች ሴቶች እየተደራጁ፣ ግጥሚያ ያዘጋጃሉ፡፡ ልክ እንደ እያንዳንዱ የወንዶች ክለብ የሴቶችን ክለብ አንዲኖር እያሰብን ነው፡፡

ህፃናቶቹ በተለይ እዚህ ሀገር የሚወለዱት በጣም ይጫወታሉ የሴቶቹን ኳስ ወደ ፊት የራሳቸውን ቲም ፈጥረው እስኪለዩ ደረስ ከእኛ ጋር አብረው እንዲካሄዱ አድርገናቸዋል፡፡

ባውዛ፡- ሴቶቹን ለማበረታት ወይንም ወደ ክለቡ እንዲመጡ የምታደርጉት የተለየ ነገር አለ?

አቶ ጌታቸው ፡- በመተዳደሪያ ደንባችን ተካቷል ሴቶችንም በተመለከተ፡፡ በየደረስንበት ሴቶች ተሳታፊ አንዲሆኑ እናበራታታለን፡፡ በአንድ ወቅት ሦስት ደርሰው ነበር፡፡ እንደ ወንዶች ክበብ አይቀጥሉም ግን … ነገር ግን በየሄድንበት ሁሉ ሴቶችም እንዲሳተፉ፣ እያንዳንዱ ክለብም የሴቶች ቡድን እንዲኖረው እያበረታታን ነው፡፡

የዘንድሮ የክብር እንግዳ ማን ናቸው?

አቶ ጌታቸው ፡- ዋናው የክብር እንግዳችን የድሮ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቡድን ተጫዋች የነበረ ፋንታ መኮነን ነው፡፡ ዛሬ በሽምግልና ዓለም ላይ ያለ ሰው ነው፡፡ ልዩ እንግዳ ብለን የመረጥናቸው ሰዎች አሉ፡፡ ዘንድሮ የመረጥነው ሻምበል ባላይነህ እና አትሌት ፈይሣ ለሊሳን ናቸው፡፡

ባውዛ፡- የኢ ኤስ ኤፍ ኤን ኤ ዓላማው ምንድን ነው?

አቶ ጌታቸው ፡- አሜሪካን የሚኖር ከተለያየ ዓለም የመጣ ነው፡፡ አብዛኛውም ሰው ከተለያየ ዓለም መምጣቱ እና በየመጣበት አካባቢና ዓለም በቡድንና በመጣበት ባህል ሁኔታ ሰለሚሰባሰብ በኳስም ይሁን በተለያዩ ማኅበረሠብ ዓቀፍ ጉዳዮች ጠንካራ እና እርስ በርስ መገናኛ ጉዳዮች አሏቸው፡፡ ልክ እንደ ግሪኮች፣ ራሺያዎች፣ ዩክሬኖች አላቸው፡፡ ኳሱ ሰበብ ሆነ እንጂ ዋናው ባህላችን ኢትዮጵያዊነታችን ነው የሚያሰባስበን፡፡ ሰው ኳስ ለማየት ብቻ ሳይሆን የቆየ ጓደኛውን ለማግኘት ነው፡፡ በዚህ ወቅት “ሪ ዩኔዬን” የሚባል አሉ፡፡ የቤተ ዘመድ፣ የፖለቲካ፣ የተማሪዎች … የመሳሰሉ ስብሰባዎች ይደረጋሉ፡፡ ሰው ይሄንንም ለማድረግ ነው የሚመጣው … ይሄን በማሰብም ሆቴል ስንከራይ አዳራሽ መኖሩን እናረጋግጣለን፡፡   ለምሳሌ ያክል የድሮ የአየር ኃይሎች ማኅበር የሚባል አለ፡፡  እነሱ ለምሳሌ በየዓመቱ ይሰበሰባሉ፡፡ በየዓመቱ ይመጣሉ፡፡ በዚህ ወቅትም የተለያዩ ነገሮችን ይወጥናሉ፡፡ አላማችን ሰውን ለማገናኘት ነው፡፡ ደግሞም ተለምደናል፡፡

ባውዛ፡- በዚህ አጋጣሚም ለጋብቻ የበቁም አሉ አሉ?

አቶ ጌታቸው ፡- አዎ፡፡ ሚስት ባል ያጋኙበት ቦታ ነው፡፡ አንዳንዶቹ አንደውም በዚህ አጋጣሚ ተዋውቀውና ተጋብተው ልጆችን ወልደው ልጆቻቸው አድገው ኳስ የሚጫዎቱበት ደረጃ የደረሱ አሉ፡፡ 34 ዓመት ቀላል አይደለም፡፡

ባውዛ፡- ከአላማዎቹ ውስጥ የኢ ኤስ ኤፍ ኤን ኤ ለማኅበረሠቡ የምታደርጉት የተለየ ነገ አለ?

አቶ ጌታቸው ፡- አዎ፡፡ ስኮላር ሺፕ ለተጫዎቾችን ሆነ ለማይጫወቱን እድል አንዲያገኙ እናደርጋለን፡፡ ሀገራዊ ጉዳይ ሲመጣ በተለያየ መልኩ እርዳታ እንዲገኝ እናመቻቻለን፡፡ እኛ የማናደርገው በሀይማኖትና በፖለቲካ ጉዳይ አንገባም፡፡

ባውዛ፡- ምን ያህል ካፒታል አላችሁ?

አቶ ጌታቸው ፡-ከእጅ ወደ አፍ ነው፡፡ ወጪያችን ብዙ ነው፡፡ ብዙ ሰው የእኛን ኦርጋናይዜሽን የሚያየው ብዙ ብር ያለን ነው የሚመስለው፡፡ የእኛ ክበብ ለሠላሳ አንድ ክለቦች ሆቴል ይይዛል፣ ስቴድየም ይከራያል፣ ለሴኪሪቲ ይከፍላል፣ ለተለያዩ …. ለፅዳት፣ ለጄኔሬተር፣ ለተጫዎቾች ኢንሹራንስ እንከፍላለን … በፊት ጊዜ ስፖንሰሮች ነበሩ ከኢትዮጵያ የሚመጡ፡፡ ከስፖንሰሮች ጠቀም ያለ ገንዘብ እናገኛለን፡፡ አሁን እንደዚህ ዓይነት ነገር ቀርቶ የምናገኘው ከበር ላይ እያስከፈልን ከምናገኘው ነው ብቻ ነው፡፡

ስለሆነም የትኬቱን ዋጋ ከመወሰናችን በፊት ወጭያችን ምንድን ነው ብለን ሂሳብ እናደርጋለን፡፡ ወጪያችንን ለመሸፋን ምን ያህል ለትኬት ማስከፈል አለብን ብለን …ይሄንንም ደግሞ ለህዝቡ እናሳውቃለን፡፡ ሰለዚህ የሄን ያህል ነው ብለን መንገር ይቸግረናል፡፡

ባውዛ፡- ከ13 ዓመት በኋላ ወደ ሲያትል ስትጓዙ ሲያትሎች አቀባበላቸው ዝግጅታቸው ምን የተለየ ነገር ሰንቀዋል?

አቶ ጌታቸው ፡- በጉጉት እየጠበቁን ነው የተለየ ነገር እንዳላቸውም እናውቃለን፡፡

ባውዛ፡- አቶ ጌታቸው ለሰጡን ቃለ ምልልስ በባውዛ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው!

መልካም በዓል  ይሁንላችሁ፡፡

Getachew Tesfay ESFNA Prisedent

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here