አንጋፋው ድምፃዊ መስፍን አበበ በ63 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ / THE LEGEND#MESFIN ABEBE passed away

0
679

አሳዛኝ ዜና

• አንጋፋው ድምፃዊ መስፍን አበበ በ63 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ / THE LEGEND#MESFIN ABEBE passed away,63.

ያዥልኝ ቀጠሮ፣ አይሽ አይሽና፣ መልካም ልደትና ሌሎችም ተወዳጅ ሙዚቃዎችን በጊታር በመጫወት የሚታወቀው ድምፃዊ መስፍን አበበ ትናንት በድንገተኛ ህመም ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ዛሬ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ገደማ ህይወቱ ማለፉን ከቤተሰቦቹ ሰምተናል፡፡

መስፍን አበበ ከደሴ ወ/ሮ ስህን ትምህርት ቤት ባንድ ጋር በመሆን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በመዘዋወር ሙዚቃዎችን ይጫወት ነበር፡፡

ቦክስ ጊታሩን በመያዝ 22 ያህል ካሴቶችን ማሳተሙን ከቤተሰቦቹ ተነግሮናል፡፡

ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ አባት የነበረው የድምፃዊ መስፍን አበበ የቀብር ስነ-ሥርዓት ነገ ከቀኑ በ6 ሰዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያ ይፈፀማል ተብሏል፡፡

መስፍን አበበ አመለጠን!

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here