ዘ-ዊኬንድ የ2016 ቢልቦርድ የሙዚቃ ሽልማትን በመውሰድ ቀዳሚነትን ተቀዳጀ!!

0
1386

በስምንት የተለያዩ ዘርፎች ሽልማት የጎረፈለት ወጣቱ አቤል ተስፋዬ(ዘ-ዊኬንድ)የ2016 የቢል ቦርድ ተሸላሚ ኮኮብ ሆኖ ተገኝትዋል፡፡ በሙዚቃ ቅንብሩ፣ በመገናኛ ብዙሃን የዘፈን ተደማጭነት እና የሙዚቃ አቀናቀን ስልቱ በመሳሰሉት ዘርፎች ከአንጋፋዎቹ መካከል በአንጸባራቂነት ደምቆ ያመሸው አቤል ተስፋዬ ስምንቱንም ሽልማቶች ለመቀበል ወደ መድረክ ሲወጣ ታዳሚዎች ከወንበራቸው እየተነሱ አድናቆትታቸውን በጭብጨባና በጩኸት ገልጸውለታል፡፡ ትናንት በላስቬጋስ በነበረው ዝግጅት የ2016ዓ.ም የቢልቦርድ ሽልማት መታዎሻነቱ፣ በቅርቡ በ57 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ለተለየው ድምጻዊ፣ የሙዚቃ ዜማና ግጥም ደራሲ ፕሪንስ ሮጀርሰን ስም ተሰይሟል፡፡በዚህ ምሽትም ኤቤል ተስፋዬ ስለሟች አርቲስት ፕሪንስ ፎጀርሰን ሳግ እየናነቀው ነበር ንግግር ያደረገው “ፕሪንስ በጣም ቅርቤ የነበረ ሰው ነበር፡፡ በስራዎቼም ከጎኔ የነበረ የሚያበረታታኝና የሚደግፈኝ ድንቅ ሰው ነበር… በህይወት ባትኖርም በልቤ ውስጥ ለዘላለም ትኖራለህ” ብሏል፡፡ ከኢትዮጵያዊ ወላጆች የተገኘውና በትውልድ ካናዳዊ የሆነው አቤል ተስፋዬ(ዘ ዊኬንድ) በአር ኤንድ ቢ የሙዚቃ ስልቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ አንቱታ የተቸረው፣ ታታሪ ወጣት አቀንቃኝ እንደሆነ የአለም መገናኛ ብዙሃንና የሙዚቃ ባለሞያዎች መስክረውለታል፡፡ አቤል ተስፋዬ(ዘ ዊኬንድ) የ2016 የቢልቦርድ ያሸነፈባቸውን የሙዚቃ ዘርፎች፡፡ Hot 100 Artist: The Weekend Top Song Sales Artist: The Weekend Top Radio Songs Artist: The Weekend Top Streaming Songs Artist: The Weekend Top R&B Artist: The Weekend Top R&B Album the Weekend, “Beauty behind the Madness” Top R&B Song: The Weekend, “The Hills” Top Streaming Song (Audio): The Weekend, “The Hills” Top Streaming Song (Video): Silentó, “Watch Me”

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here