Yehunie Belay “GUZARA”New CD Release Party – የይሁኔ በላይ አዲስ አልበም በDecember,16,2014 Alexandria VA. ይመረቃል!

0
4231

 

አርቲስት ይሁኔ በላይ ከዚህ በፊት ባሳተማቸዉ ስምንት አልበሞች በልዩ ቅላጼዉ በሚያዜማቸዉ ዘፈኖች ባህልን ቌንቋን ታሪክንና ፍቅርን በሚያንጸባርቁ ልዩና ተወዳጅ በሆነዉ ድምጹና በመልካም ስነ ምግባሩ አንቱ የተሰኜዉ ድምጻዊ ነዉ::

ከአምስት ዓመት የፈጠራ ጊዜ በኌላ ዘጠነኛዉን አልበሙን “ጉዛራ” በሚል ርዕስ ለአድናቂዎቹ ሊያበረክት ቀን ቆጥሮ ዝግጅቱን አጠናቋል።

በዚህ አልበም ዉስጥ ጣፋጭና ተወዳጅ ዜማዎችን በልዩ ልዩ መልዕክት አዘል ግጥሞች የተቀነባበሩ ሲሆን ደራሲዎች 1) አበበ ብርሃኔ 2) ተስፋ ብርሃን 3) ተዘራ ተችሎ 4) አዱኛ ቦጋለ 5) እዮብ ብርሃኑ  6) አስማማዉ በለዉ 7) አንለይ የሽወንድ እና እንዲሁም በራሱ በድምጻዊዉ የተደረሱ ዜማና ግጥሞችም ተካትተዋል::

ይህንን አስር ዘፈኖችን የያዘዉን አዲስ አልበም ሙዚቃዉን ያቀነባበረዉ ታዋቂዉ አቀናባሪ ሄኖክ ነጋሽ መሆኑንም ድምጻዊዉ ለባዉዛ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ገልጿል::

ለዚሁም ለዛሬዉ በምርቃቱ እለት በይፋ ከሚደመጠዉ ዘፈኖቹ ዉስጥ አንዱን “ምስጋናዉ ደግ ነዉ” የተሰኜዉን ዜማ በፎቶ ምስል የተቀነባበረዉን ጣፋጭና ቁም ነገር አዘል ዘፈን እንካችሁ ብሎናል::

መልካም ድምጫ!

በዕለቱ ማክሰኞ  : December,16,2014

        Place: MEAZA RESTAURANT

        Addressee: 5700 Columbia Pike Alexandria VA

         Time: Door opened @ 7pm

በዕለቱም ታላላቅ አርቲስቶች እንኴን ደስ አለህ ሊሉትና ምሽቱንም የተለያዩ ዘፈኖችን እየተጫወቱ ታዳሚዉን የሚያስደስቱ መሆኑን እየገለጹ መሆናቸዉን አርቲስት ይሁኔ በላይ ተናግሯል:: በመሆኑም እኛም የባዉዛ ጋዜጣ የዝግጅት ክፍል ባልደረቦች በምሽቱ አብረን የምንገኝ መሆኑን ስንገልጽ በደስታ ነዉ:: ለአንባቢዎቻችንም ይህ ታሪካዊ ምሽት እንዳያመልጣችሁ እንመኛለን::

እዚያዉ እንገናኝ!!!

 በመላዉ ዓለም ለምትገኙ የይሁኔ በላይ አድናቂዎች ከDecember,16,2014 በኌላ cdbaby.comhttp://www.cdbaby.com/cd/yehuniebelay2 እየገባችሁ መግዛት ትችላላችሁ!

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here