“ለብዙ ወጣቶች የትምህርት ስኮላርሽፕ መስጠት ስለቻልን ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል” ወ/ሮ የሽመቤት በላይ(ቱቱ)

0
3146

በ 1993 ዓም  የኢትጵያውያን ንግድ ድርጅቶች፣አገልግሎት ሰጭዎች፣ማህበራት በ አጠቃላይ የ ኢትዮጵያውያኑን ማህበረሰብ እርስ በርስ እንዲሁም ከ ሌላው ማህበረሰብ ጋር መረጃ የሚለዋወጥበት መድረክ ለመፍጠር ታስቦ  የ ተቋቋመው የ ኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ እነሆ ድፍን ሃያ አመት ሞላው::

የኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ መስራች እና ፕሬዝዳንት ወ/ሮ የሽመቤት በላይ(ቱቱ) ስለ የሎው ፔጁ ሲና ገሩ “ የኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ የአለፉት ሃያ አመታት የስኬት ጉዞ የማህበረሰቡ የስኬት ጉዞ አድርጌ ነው የምቆጥረው” ይላሉ::

“የኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ ማህበረሰቡን እርስበርስ ከማቀራረብ በተጨማሪ፣ የማህበረሰባችንን ጠንካራ ሰራተኛነት ማንነት በመንግስት ደረጃ ሳይቀር እውቅና ያሰጠ አንዱ ትልቁ ድርጅት ነው”

በ 2011 ዓም የ ዋሽንግተን ዲሲ ካውንስል መስከረም 15፣2011 ቀን “የኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ ቀን” ብሎ ወስኗል:: በተጨማሪም  የ ዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ  ቪንስ ግሬይ “ መስከረም 13፣2014 ቀን በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤክስፖ ቀን” ብለው  አውጀዋል::

ይንን አስመልክቶ  ወ/ሮ ቱቱ ሲናገሩ “ በእነዚህ እውቅናዎች የሚሰማኝ ደስታ እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው፣ ይሄ እውቅና ኢትዮጵያን ያስጠራ ድርጊት ስለሆነ በጣም ደስ ብሎኛል፣ እውቅናው ለእኛ ይሰጥ እንጂ   በማህበረሰባችን ስም ነው የተቀበልነው ስለዚህ ሁላችንም ልንኮራ ይገባል”::

ለስምንተኛ ጊዜ የተከበረው የኢትዮጵያ ኤክስፖ፣ የ ኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ የቆመለትን የማህበረሰቡ አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ የመሆን አላማ የሚደግፍ ነው:: የ ኢትዮጵያ ኤክስፖ ማህበረሰቡን እርስበርስ እንዲሁም ከአገልግሎት ሰጭዎች ጋር በቀጥታ እንዲገናኝ እድሉን መፍጠር አላማው አድርጎ ነው የሚንቀሳቀሰው::

ባለፉት አመታት የኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ በኢትዮጵያውያን ወጣቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል:: የኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ የ ኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበራትን ከማበረታታት እና በመደገፍ ጀምሮ  ከማህበረሰቡ ጋር እንዲገናኙ እድሉም በመፍጠር አገልግሏል”::

ወ/ሮ የሽመቤት አያይዘውም “የኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ ለኢትዮጵያ ወጣቶች የመረጃ ምንጭ ከመሆን ጀምሮ  አሁን ደግሞ ለ ወጣቶች የነጻ የትምህርት እድል የሚያፈላልግ ተቋም እየሆነ መጥቷል:: በስምንተኛው የ ኢትዮጵያ ኤክስፖ እዲሁም በ ሃያኛው የኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ  ከብረ በዓል ላይ የኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ  በቁንጅና ውድድር አሸናፊ ለሆኑ ወጣት ኢትዮጵያውያን የነጻ የትምህርት እድል እንዲሰጥ አድርጓል:: በተመሳሳይም ከዚህ በ ፊት በተከናወኑ ኤክስፖዎች ላይ ለብዙ ወጣቶች ስኮላርሽፕ እንዲያገኙ አድርገናል:: ከዚህ በ ፊት በኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ አማካኝነት ስኮላርሽፕ ካገኙ ተማሪዎች አንዳንዶቹ ትምህርታቸውን አጠናቀው ተመርቀዋል:: ይህንን ሳይ ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል::”

“ የማህበረሰብ ስራ  የአንድ ድርጅት ወይም ግለሰብ ስራ ሊሆን አይችልም፣ ስለዚህ ሁሉን ሰው ያካተተ ፕሮግራም ያስፈልጋል፣እዚህ ሃገር የሚወለዱ ልጆች እና ወጣቶች ባህላቸውን ይዘው እንዲያድጉ፣ከታላላቆቻቸው እንዲማሩ እንዲሁም ያሳደጋቸውን ማህበረሰብ ተመልሰው ማገልገል እንዲችሉ ለማድረግ እድሉን ለመፍጠር ስንሰራ ቆይተናል ወደ ፊትም እንሰራለን:: ከ እኛጋር በወጣቶች ዙሪያ ሊሰሩ የሚፈልጉ ማንኛውም አይነት ግለሰብ፣ ተቋም ወይም ማህበር ካለ በራችን ክፍት ነው በማንኛውም ሰአት መጥተው ሊያነጋግሩን ይችላሉ::” ይላሉ ወ/ሮ የሽመቤት::

በመጨረሻም ወ/ሮ የሽመቤት “የኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ የ ሃያ አመት የስኬትጉዞ  አጋር ለነበሩ ግለሰቦች፣ ድርጂቶች፣ አገልግሎት ሰጭዎች ከልብ የሆነ ከፍተኛ ምስጋናየ ይድረሳችሁ” ብለዋል::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here