Exclusive Interview with Dr.Anteneh Roba ከ ዶ/ር አንተነህ ሮባ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ

0
812

ባውዛ: ከባውዛ ጋዜጣ ጋር ቃለ ምልልስ ላማድረግ ጊዜዎን ስለሰጡን በጣም እናመሰግናለን::

ዶ/ር አንተነህ:  ስለ ጋበዛችሁኝ እኔም በጣም አመሰግናለሁ::  ስሜ አንተነህ ተስፋዬ ሮባ ነው:: አሜሪካን ሃገር በ ሂዮስተን ከተማ ለ 19 አመታት በህክምና ሙያ ላይ ቆይቼ በ ቨርጂኒያ ስቴት በቅርቡ አዲስ ቢሮ ከፍቻለሁ::

ባውዛ: ከባውዛ ጋዜጣ ጋር ቃለ ምልልስ ላማድረግ ጊዜዎን ስለሰጡን በጣም እናመሰግናለን::

ዶ/ር አንተነህ:  ስለ ጋበዛችሁኝ እኔም በጣም አመሰግናለሁ::  ስሜ አንተነህ ተስፋዬ ሮባ ነው:: አሜሪካን ሃገር በ ሂዮስተን ከተማ ለ 19 አመታት በህክምና ሙያ ላይ ቆይቼ በ ቨርጂኒያ ስቴት በቅርቡ አዲስ ቢሮ ከፍቻለሁ::

ባውዛ: የት ነው ተወልደው ያደጉት?

ዶ/ር አንተነህ: የተወለድኩት አዲስ አበባ ነው:: አባቴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የ ኢትዮጵያ ልኡክ አባል ስለነበር በ መጀመሪያ ኒውዮርክ ከዛም ዋሽንግተን ዲሲ ኖረናል::  ኢትዮጵያ ከአያቶቼ ጋር እየኖርኩኝ ሃይስኩል ጨርሼ  ወደ አሜሪካን ሃገር ተመለስኩኝ::

ባውዛ: ወደህክምና ሙያ እንዴት ገባህ?

ዶ/ር አንተነህ: አባቴ ነው ወደዚህ ሙያ እንድገባ የገፋፋኝ:: እናቴ  ገና ልጅ እያለሁ ስለሞተች አባቴ ሁልጊዜ ህክምና ካጠናህ የናትህን በሽታ ማወቅ ትችላለህ ይለኝ ነበር:: በልጅነቴ ስቴትስኮፕ ገዝቶ  ሰጥቶኝ ደረቱላይ እያደረኩ እንዳዳምጥ ያደርገኝ ነበር::

ባውዛ:  የህክምና ትምህርት የት ሃገር ተከታተሉ? አሁን ወዳሉበት የ ፋንክሽናል ህክምና እንዴትገቡ?

ዶ/ር አንተነህ: አሜሪካን ሃገር ኖርዝ ካሮላይና ዴቪድሰን ኮሌጅ ስማር ቆይቼ በስኮላርሽፕ ችግር

ምክንያት አቋረጥኩ:: ሮማንያ የሚባል ሃገር ለትምህርት አመለከትኩ እና ተቀበሉኝ

ከዛም በ ሜዲካል ዶክትሬት ዲግሪ ጨርሼ በ 1982 ተመረኩ:: ከዛም ወደ አሜሪካን

ሃገር መጥቼ ሬዚደንስ ሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ በኢመርጀንሲ ሜዲሲን ሰራሁ:: ለ ሃያ

አመት በህክምና ሙያየ ውስጥ ለክሮኒክ በሽታ ታማሚዎች ነባሩ

የህክምና አሰጣጥ የበሽተኞችን ህይወት ሲለውጥ ማየት ስላልቻልኩ ከ

ነባሩ(conventional Medicine)  ወደ Funcational Medicine ዞርኩ:: በ ኤስቴቲክ

ሜዲሲን ቦርድ ሰርቲፋይድ ሃኪም ሆኜ እየሰራሁ እገኛለሁ:: አሁን ደግሞ በፋንክሽናል

ሜዲሲን ወይም አንታይ ኤጂንግ ይሉታል ፌሎውሽፕ እየሰራሁ ነው በተጨማሪም በ

ኦቢሲቲ ህክምና ስልጣና ወስጃለሁ ነው::

ባውዛ: አሁን “ዚኒያ” የሚባል የራስዎ ክሊኒክ በፌየርፋክስ ቨርጂኒያ ከፍተዋል ምን አይነት

የህክምና አገልግሎት ይሰጣሉ?

ዶ/ር አንተነህ: በዋናነት የምንሰራው በሽታ ከመጀመሩ  በፊት ማስቀረት ወይም ማስቆም የሚቻልበት መንገድ ወይም የፋንክሽናል ህክምና አልግሎት ነው:: ላለፉት ሃይ ዓመታት በህክምና ሙያ ውስጥ ስሰራ ዛሬ ያከምናቸው ሰወች በ ወር ውስጥ እንደገና ታመው ይመጣሉ፣ ክሮኒክ በሽታ ያላቸው ሰወች ደጋግመው ይታመማሉ ህይወታቸው እንዲቀጥል ማድረግ እንጂ ኳሊቲ ያለው ህይወት እንዲመሩ ማድረግ አይችልም ልማዳዊው ህክምና፣ functional Medicine እነዚህ ክሮኒክ በሽታወች ከመጀመራቸው በፊት ገና ከመጀመሪያ ማስቀረት የሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ነው የምንሰራው::

እነዚህ ክሮኒክ በሽታወች ከመጀመራቸው አስቀድሞ የሚታዩ ምልክቶች አሏችው:: ሙሉ ጤነኛ የሚመስሉ ሰወች፣ ለሌላ በሽታ የመጡ ሰወች ላይ የደም የስኳር መጠናቸው የተዛባ ሆኖ እናገኛቸዋለን::

ፋንክሽናል ህክምና የበሽታ ስታንዳርድ ከፍተኛ ነው:: በተራው ህክምና ጤነኛ ነው የሚባል ሰው በፋንክሽናል ህክምና  ስታንዳርድ መለኪያ ችግር ሊያሳይ ይችላል፣ ማድረግ ያለባቸው እና የሌለባቸውን ነገሮች ስለምንነግራቸው በሽታወችን አስቀድመን መከላከል እንችላለን::

የተለምዶው ህክምና ሰውነትን ከፋፍሎ ነው የሚያየው፣ ሃኪሞች አንዱ የልብ ስፔሻሊስት ነው ፣ሌላው የሳንባ ስፔሻሊስት ነው ወዘተ ሰውነታችን ግን አንድ አካል ነው እርስ በርስ የተያያዘ ነው ስለዚህም ሁሉን ያካተተ ህክምና ያስፈልገዋል:: የኛህክምና ደግሞ ይህንን ያስቺለናል::

ባውዛ: አንድ ሰው ወደ እናንተ ክሊኒክ መምጣት ያለበት መች ነው? ምንም አይነት የህመም ምልክት ያላቸው ሰወች መምጣት ይችላሉ?

ዶ/ር አንተነህ: ማንኛውም ሰው መምጣት ይችላል! ማንኛውም ስለጤናው ግድ የሚለው ሰው በሙሉ መምጣት ይችላሉ:: አንድ ሰው ምንም ሳይሰራ ድካም ሲሰማው፣ ራስ ምታት ሲኖረው እና ተመሳሳይ ነገሮች ሲሰማው፣ አንድ ጤነኛ የነበረ ሰው ሰውነቱ ውስጥ መግለጽ የማይችለው ለውጥ ሲያሳይ ወዘተ ድንገት በጠና ታሞ  ኢመርጀንሲ ሩም  ከመሄዱ በፊት ቀደም ብሎ ማወቅ ከፈለገ፣መምጣት ይችላል ሌላ የጠና በሽታ  ሆኖ ከመታየቱ በፊት መፍትሄ ማግኘት የ ሚፈልግ ሰው ሁሉ እኛ ጋር መምጣት ይችላል::

ከዚህ በተረፈ ማንኛውም አይነት የክብደት ችግር ያለባቸው፣ የደም ግፊት ችግር ያለባቸው፣ በቤተሰባቸው የስኳር በሽታ፣ካንሰር እና ሌሎች ተመሳሳይ በሽታ ያለባቸው ሰወች ጤናቸውን በቅርበት መከታተል ስለሚኖርባቸው እኛ ጋር ሊመጡ ይችላሉ::

የእኛ የህክምና ፍልስፍና ሮጦ መድሃኒት መስጠት አይደለም፣ ታካሚው የአኗኗር ዘይቤውን ቀይሮ በሽታውን ማስቀረት የሚቻልበት መንገድን ማሳየት ነው፣ የበሽታውን ስር-መሰረት(root cause) ለይተን እሱን የማከም ስራ ነው የምንሰራው:: አመጋገብ ብዙወቻችን በሽታወች ሊያስቀር ይችላል፣ነገር ግን ሃኪሞቻችን የአመጋገብ ትምህርት ስላማይወስዱ ስለ አመጋገብ ምንም አይነት ምክር ለበሽተኞቻቸው አይሰጡም፣ በጣም ብዙዎቹ ክሮኒክ በሽታወች የሚመጡትም የሚፈወሱትም ከአመጋገብ ጋር በተያያዘ ጉዳይ ነው፣ ስለዚህ ትክክለኛውን አመጋገብ መከተል እነዚህን በሽታወች ከመከላከል እና ከመፈወስ አንጻር ጥቅም አለው::

ወደ ፉንክሽናል ህክምና ከመግባቴ በፊት ሰወች ቫይታሚን ሲውጡ ጥቅም የለውም ብየ አስብ ነበር፣ አሁን ግን ያለኝ አመላካከት ተቀይሯል፣ የምንኖርበት አካባቢ በመርዛማ በካዮች የተበከለ ነው፣ሰውንታችን ይሄንን መቋቋም የሚችልበት አቅም ለመስጠት እነዚህን ንጥረ ነገሮች ከ ሰፕሊመንትስ ማግኜት ያስፈልገናል:: ለምሳሌ አንታይ ኦክሲዳንቶች ያስፈልገናል ነገር ግን በቂ አንታይ ኦክሲዳንት ለማግኔት ቀኑን ሙሉ ብሉቤሪ ስትበላ ካልዋልክ ወይም በቀን 6 ጋሎን ግሪንቲ ካልጠጣህ በስተቀር ሰውነት የሚፈልገውን በቂ መጠን አታገኝም ስዚህ ሰፕሊመንት መውሰድ ያስፈልጋል::

ባውዛ: ከፍተኛ ጤንነትን ለማጠበቅ አንድ ሰው በአጠቃላይ ምን ማድረግ አለበት ብለው ይመክራሉ?

ዶ/ር አንተነህ: መደረግ ያለባቸው ብዙ ነገሮች አሉ፣ በአጠቃላይ ግን ጥሩ አመጋገብ፣ የአኗኗር ዘይቤን መቀየር፣ መርዛማ የሆኑ ነገሮችን ለምሳሌ አልኮል፣ ሲጋራ፣ እጾችን ወዘተ ማስወገድ፣ ከሰወች ጋር መልካም ግንኙነት መመስረት፣ ጭንቀትን መቀነስ፣ ጤናማ መንፈሳዊ ህይወት እንዲኖረን ማድረግ ለምሳሌ መጸለይ፣ሜዲቴት ማድረግ፣ዮጋ መስራት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት፣ ሰፕሊመንትስ መውሰድ፣ጤናን በቅብ መከታተል::

ባውዛ: የኮስሞቲክ ህክምናን እንደ ቅንጦት ህክምና የማየት ነገር አለ እርስዎ እንዴት ያዮታል? የህክምና አገልግሎታችሁ ምን ያክል ውድ ነው? ምን አይነት ኢንሹራንሶችን ትቀበላላችሁ?

ዶ/ር አንተነህ: ህክምናችን ብዙም ውድ አይደለም:: ኮስሞቲክ ህክምናው ለሁሉም ሰው አይደለም:: አንድ ሰው ፊቱ በብጉር የተወረረ ሰው ከብጉሩ ጋር መኖር ይችላል፣ ነገር ግን ብጉሩን ለማስወገድ ህክምና ቢያስፈልገው ቅንጦት ነው? ወይስ አይደለም የሚለውን ሰውየው ነው የሚያውቀው፣ ስለዚህ ኮስሞቲክ ህክምና የቅንጦት ህክምና ነው የሚባለው እንደተመልካቹ ነው::

የ ፋንክሽናል ህክምናው ግን በጣም አስፈላጊ ነው፣ ህክምናችን ከ ሌላው የተራ ህክምና  ውድ አይደለም ነገር ግን ምንም አይነት ኢንሹራንስ አንቀበልም:: ነገር ግን የ ፋንክሽናል ህክምና ከረዥም ጊዜ አንጻር ብዙ ብር ያተርፍልናል፣ በተጨማሪም ጤናማ ህይወት እንድንኖር ያደርገናል::

ማንም ሰው መጥቶ  ምክር ማግኜት ይችላል፡: እኛ የምናዛቸው እና የምንሰራቸው የደም ቴስቶች ብዙዎቹ ሃኪሞች የሚያዟቸው አይነት አይደሉም:: ለምሳሌ  እኛ የሆርሞን ምርመራ እናዛለን::  እድሜህ በገፋ ቁጥር የሆርሞንመጠን እየቀነሰ ይሄዳል፣ ከዛጋር ተያይዞ የሚታዮ የሰውነት ለውጦች ይኖራሉ ያንን ማስተካከል ከፍተኛ የጤና ጥቅም አለው:: ለምሳሌ ቴስቶስትሮን የወንዶች ሆርሞን ነው፣ ከ 30 አመት በኋላ  በከፍተኛ ፍጥነት መቀነስ ይጀምራል ያደግሞ ከፍተኛ የሆነ የጤና መዛባት ያስከትላል፣ ይህንን ሆርሞን መተካት ከፍተኛ የሆነ የጤና መዛባትን ይከላከላል ማለት ነው::

ኤስትሮጂን የሴቶች ሆርሞን ነው፣ አንድ ሴት ፔሬድ ማየት ስታቆም ጀምሮ  የኤስትሮጅን መጠን ማሽቆልቆል ይጀምራል፣ ኤስትሮጂን ሴቶች ሰውነት ውስጥ 400 የሚደርሱ ጥቅሞች አሉት፣ እነዚህ ሁሉ ጥቅሞች ይቀራሉ ማለት ነው:: ስለዚህ እነዚህ ሆርሞኖችን መተካት  የጤናን ሁኔታ በ ከፈተኛ ደረጃ ያሻሽላል ማለትነው::

ባውዛ:  ዶ/ር አንተነህ ጊዜዎን ስለሰጡን በአባቢዎቻችን ስም አመሰግናለሁ

ዶ/ር አንተነህ: እኔም በጣም አመሰግናለሁ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here