“መስከረም 13፣2014 በዋሽንግተን ዲሲ የ ኢትዮጵያ ኤክስፖ ቀን ተብሎ ታውጇል!” ከንቲባ ቪንሰንት ግሬይ

0
3401

በ ኢትዮጵያ የሎውፔጅስ  20ኛ ዓመት በዓል እንዲሁም፣ ስምንተኛው የ ኢትዮጵያ ኤክስፖ አመታዊ ፕሮግራም ላይ የዋሽንግተን ዲሲው ከንቲባ ቪንሰንት ግሬይ፣ የ ዲሲ ካውንስል አባል ጂም ግርሃም እንዲሁም ኮሚሽነር  አሌክስ ፔድሮ ተጋባዝ እንግዶች የነበሩ ሲሆን ቢዝነስ ማህበረሰቡ አባላት እንዲሁም በመቶዎች የሚቆጠሩ ከዋሽንግተን ዲሲ ሜትሮ አካባቢ በመጡ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት በ መስከረም 13 ቀን 2014 በኦምኒ ሸርሃም ሆቴል ተከብሯል::

በዝግጂቱ ላይ የንግድ ድርጂቶች፣ አገልግሎት ሰጭዎች እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች እራሳቸውን ለታዳሚዎች እና እርስ በርስ ያስተዋዎቁበት ደማቅ የኤክስፖ ፕሮግራም ተካሂዷል:: በኤክስፖው ላይ ከ ሰባ በላይ የንግድ ድርጅቶች፣ አገልግሎት ሰጭዎች እና ግብረ ሰናይ ድርጂቶች ተሳተፈዋል::

የምሽቱን የመዝናኛ ፕሮግራም የፕሮግራሙ አዘጋጅ ና የኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ ፕሬዝዳንት  አዘጋጅ ወ/ሮ የሽመቤት በላይ(ቱቱ) በንግግር ከፍተዋል:: በ መቀጠልም የአዲስ አመት እንቁጣጣሽ (እዮሃ አበባዮ) ዘፈን በአርቲስት ይሁኔ  በላይ ከ ራስ ባንድ ጋር በ መሆን በደመቀ ሁኔታ ቀርቧል::

የኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ ሃያኛ አመት እንዲሁም ስምንተኛውን የ ኢትዮጵያ ኤክስፖ በማስመልከት ለማህበረሰቡ የቅርብ ወዳጅ ለሆኑት የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ ቪንስ ግሬይ፣ የ ካውንስል አባል ጂም ግርሃም እና  ለ ኮሚሽነር አሌክስ ፔድሮ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል::

የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ የሆኑት ቪንሰንት ግሬይ፣ በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ከንቲባው በነበራቸው “One City” ወይም “አንድ ከተማ” እቅድ ውስጥ ኢትዮጵያዊ-አሜሪካውያኑን በፕሮግራማቸው ላይ በማካተታቸው፣ እንዲሁም በስልጣን ዘመናቸው ኢትዮጵያዊ-አሜሪካውያን ቢዝነሶች ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች አፋጣኝ መልስ በመስጠት እና እንዲሰጥ ባማድረግ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ማህበረሰቡን በመወከል የ ኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ የሽመቤት በላይ(ቱቱ) ለከንቲባው “Award for outstanding service to the Ethiopian American community of the DC” በሚል ልዮ ስጦታ አበርክተውላቸዋል::

ከንቲባ ቪንሰንት ግሬይ ሽልማቱ ስለተሰጣቸው በጣም አመስግነው ኢትዮጵያ-አሜሪካውያኑ ማህበረሰብ በጣም ጠንካራ ሰራተኛ  በመሆን ለ ዋሽንግተን ዲሲ እድገት እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ አጉልተው ምስጋናቸውን ገልጸዋል:: እንዲሁም የ ኢትዮጵያ የሎውፔጅስ እና ኢትዮጵያ ኤክስፖ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ እርስበርስ እንዲሁም ከ ሌላው ማህበረሰብ እና ቢዝነሶች ጋር በማቀራረብ እየተጫወተ ያለውን ትልቅ ሚና አንስተዋል:: በቀጠልም ከንቲባው ይህንን ለማህበረሰቡ እና  ቢዝነሶች ያለውን አስተዋጽኦ እውቅና ለመስጠት መስከረም 13 ቀን 2014 ዓም “የ ኢትዮጵያ ኤክስፖ ቀን” ተብሎ በዋሽንግተን ዲሲ ታውጇል! ብለው ገልጸው ይህንን የሚደነግገውን አዋጅ የምስክር ወረቀት ለ ኢትዮጵያ የሎውፔጅስ ፕሬዝዳንት እና የኤክስፖው ዋና አዘጋጅ ወ/ሮ የሽመቤት በላይ(ቱቱ) አበርክተዋል::

በመቀጠልም ዋርድ አድን በመወከል የዲሲ ካውንስል አባል ጂም ግርሃም በዋርድ አንድ እንዲሁም በአጠቃላይ በዋሽንግተን ዲሲ ሊሚገኙ ኢትዮጵያውያን ግለሰቦች እና ቢዝነሶች ላበረከቱት አስተዋጽኦ እንዲሁም በዋሽንግተን ዲሲ ካውንስል ውስጥ የኢትዮጵያውያን ጉዳይ እንዲሰማ ላደረጉት ጥረት በአጠቃላይ ከኢትዮጵያውያኑ ማህበረሰብ ጋር ላላቸው ወዳጅነት የ ህይወት ዘመን የ ክብር ሽልማት ኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ ፕሬዝዳንት እና የኤክስፖው ዋና አዘጋጅ ወ/ሮ የሽመቤት በላይ(ቱቱ) እጅ ተቀብለዋል::

ካውንስል አባል አቶ ጅም ግርሃም ሽልማቱ ስለተሰጣቸው የተሰማቸውን ታላቅ ክብር  በመግለጽ የኢትዮጵያውያኑ ማህበረሰብ ወክለው  በማገልገላቸው የተሰማቸውን ኩራት ገላጽዋል:: አያይዘውም የ ዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ ቪንስ ግሬይ በመከተል የዋሽንግተን ዲሲ  ካውንስሎች ምክርቤ አባላት የኢትዮጵያ የሎውፔጅስ  እና ኢትዮጵያን ኤክስፖ ማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን አገላግሎት እውቅና ለመስጠት ያስተላለፉት የ ሁሉም ካውንስል አባላት ፊርማ ያለበትን ድንጋጌ የተሰጠበትን የምስክር ወረቀት ለ ወ/ሮ የሽመቤት በላይ(ቱቱ) አበርክተዋል::

የ ካውንስል አባል ጂም ግርሃም የኢትዮጵያ አሜሪካውያን ማህበረሰቡን “ለውጥ ፈጣሪዎች” ሲሉ አሞካሽተው ለ ዋርድ አንድ እንዲሁም በአጠቃላይ ለ ዋሽንግተን ዲሲ  እድገት እያበረከቱ ያለውን አስተዋጽኦ በእጂጉ አድንቀዋል::

ሶስተኛው የሽልማት ተቀባይ ኮሚሽነር አሌክሳንደር ፔድሮ ናቸው:: ኮሚሽነር አሌክስ ፔድሮ   በሾው ሜይን አካባቢ እንዲሁም በአጠቃላይ በዋሽንግተን ዲሲ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቢዝነሶች ላለፉት አስር አመታት በላይ ለሰጡት ድጋፍ እውቅና ለመስጠት ሽልማት ተሰጥቷቸዋል

ሽልማቱን ሲቀበሉ ለወ/ሮ ቱቱ እንዲሁም ለኢትዮጵያን ቢዝነስ ባለቤቶች በአጠቃላይ ምስጋናቸውን አቅርበዋል:: ኮሚሽነር አሌክስ  ከኢትዮጵያውያን ባህል የምወደው ኢትዮጵያውያን ጓደኞቻቸውን እንደ ቤተሰብ ነው የሚያዮት ብለዋል:: ስለዚህ ይህ እውቅና  በቤተሰቦቼ የተሰጠኝ እውቅና  አድርጌ ነው የምቆጥረው ብለዋል::

የልጆች ሃሁ ውድድር እና የልዮ ችሎታ ውድድር ለብቻው በተዘጋጀላቸው አዳራሽ ውስጥ ወላጆች በተገኙበት ተከናውኗል:: የ ልጆች ሃሁ ውድድር አሸናፊ የሆነችው ህጻን ማክዳ ተስፋዬ  እና የልዮ ችሎታ ውድድሩን በአስደናቂ የውዝዝዋዜ ችሎታዋ ያሸነፈችው ህጻን ሄልዳና አብይ በምሽቱ ፕሮግራም ላይ ከኢትዮጵያ የሎው ፔጅስ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ የሽመቤት በላይ(ቱቱ) እጅ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል::

በምሽቱ ከተከናወኑ ፕሮግራሞች መካከል እጅግ በጣም አጓጊ የነበረው የቁንጅና ውድድር ነበር:: የውድድሩን ማጣሪያ አልፈው ለመጨረሻው ውድድር በቀረቡት አራት ተወዳዳሪወች መካከል የተደረገው ፉክክር የተመልካቹን ቀልብ የገዛ ነበር::

ነጃጅቱ በተለያዮ ልብሶች ተውበው  ወደ መድረክ ደጋግመው ወጥተዋል፣ ውድድሩን ለማሸነፍ ያስችለናል ያሉትን  ያላቸውን ልዮ ችሎታ (talent) በየመሃሉ አቅርበዋል::

በመጨረሻም ተመልካቹ በጉጉት ሲጠባበቁት የነበረው ሰአት ማለትም ውድድሩን በዳኝነት የመሩት አራት ዳኞች  የውድድሩን አሽናፊ የሚያሳውቁበት ሰአት ደረስ:: ውድድሩን በዳኝነት የመሩት ዳኞች የሞንጎመሪ ኮሌጅ ተማሪ እና የሃያ አራት አመት ወጣት የሆነቺውን ሩሃማ ሃይሌን አሸናፊ አድርገው መርጠዋል:: የ አስራ ሰባት አመት ወጣት እና የ ኤመርሰን ሃይስኩል ተማሪ የሆነቺው  ሄራኒ በቀለ ሁለተኛ ሆና ተመርጣለች:: ውድድሩን በሶስተኛነት ያሸነፈችው የ አስራ ሰባት አመት ወጣት እና የ ካልቪን ሃይስኩል ተማሪ የሆነችው አብነት ሃይለየሱስ ነበረች::

ውድድሩን በአንደኝነት ላጠናቀቀችው ወ/ሪት ሩሃማ ሃይሌ ከ Turkish Airlines ወደመረጠችው ወደ ማንኛውም ሃገር መሄድ የሚያስችላት የደርሶ መልስ የ አውሮፕላን ትኬት ተሸልማለች:: በተጫማሪም የ American College of Commerce and Technology(ACCT) $ 14, 000 የሚገመት የሁለት አመት የ ኮሌጅ  የትምህርት ስኮላርሽፕ ሰጥቷታል::

በውድድሩ ሁለተኛ ለወጣችው ሄራኒ በቀለ ዳታ ግሩፕ የ ቴክኖሎጂ ትምህርት ቤት $13,000 የሚገመት የትምህርት ስኮላርሽፕ አበርክቶላታል:: በ ውድድሩ ሶስተኛ ለወጣችው አብነት ሃይለየሱስ ደግሞ  አሜሪካን ስኩል ኦፍ አይቲ  $700 የ ሚገመት የትምህርት ስኮላርሽፕ ተሸልማለች::

ድምጻውያን ሃይልዬ ታደሰ፣ ይሁኔ በላይ እና ደሳለኝ መልኩ ከራስ ባንድ ጋር በመሆን እንዲሁም በውዝዋዜ ጥበብ እውቁ ተወዛዋዠ አቢዮት(ካሳነች)   በደማቅ የሙዚቃ ፕሮግራም ታዳሚውን አዝናንተዋል::

በ ድንቅ የውዝዋዜ ችሎታው የሚታወቀው አቢዮት(ካሳነች)፣ አርቲስት ፍቅርተ እንዲሁም የ አርቲስት ይሁኔ በላይ እና የ ወ/ሮ  የሽመቤት በላይ የመጀመሪያ ልጅ  የሆነው ፍቅር ይሁኔ ተማልካቹን በውዝዋዜ ሲያዝናኑ አምሽተዋል:: ፍቅር ይሁኔ ባሳየው የእስክስታ ችሎታ ታዳሚውን ሲያስደምም ታይቷል::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here