Exclusive Interview with Artist Wosene Kosrof

0
1209

 

በልዮ የአሳሳል ጥበቡ ከሚታወቀው ከአርቲስት ወሰኔ ኮስሮፍ ጋር የተደረገ ቃለምልልስ

– ጠጅ ለምንድን ነው ቢጫ ሆኖ የቀረው? ለምን ሰማያዊ አይሆንም?

– ልጆችህ ላይ አገራችሁ ይሄ ነው ብለህ አትጭንባቸውም ነገር ግን ከባህሉ ቋንቋ ጋር ማስተዋወቅ ነው ያለብን::

– ሰአሊወቻችን በአለም አቀፍ ደረጃ ባህላችንን እና ቅርሶቻችንን ማውጣት አለባቸው:

 

ባውዛ፦ አርቲስት ወሰኔ ውድ ጊዜህን ሰውተህ ለቃለ ምልልስ ፈቃደኛ ስለሆንክ በ አንባቢዎችን ስም ከፍተኛ ምስጋናየን በቅድሚያ

ልገልፅ እወዳለሁ።

ወሰኔ፦ እኔም በጣም አመሰግናለሁ።

ባውዛ፦ የት ነው ተወልደህ ያደግከው?

ወሰኔ፦ አራት ኪሎ ብርሃን እና ሰላም አካባቢ ነው ተወልጄ ያደግኩት

ባውዛ፦ ወደ ስዕል ሙያ እንዴት ገባህ?

ወሰኔ፦ ኮከበ ፅብሃ ት/ቤት የአንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁኝ ክፍል ውስጥ እየወጣሁ ጥቁር ሰሌዳ ላይ ጎጆ ቤት፣ አበባ እስል

ነበር፣  አስተማሪዬም እርሳስ ሸለሙኝ ሳቅ ። ከዛም ቤቴ ሆኜ ስዕሎችን እያመሳሰልኩ ኮፒ ማድረግ ስጀምር ይሄን ያዬ

ታላቅ   ወንድሜ ያበረታታኝ ጀመር፤ አራት ኪሎ የስነጥበብ ትምህርት ቤት እንድወዳደር ገፋፋኝ በመጀመሪያ

የማልፍ   አልመሰለኝም ነበር ውጤት ተለጥፎ ሲወጣ   ከተወዳደርነው 48 ተማሪዎች ሁለተኛ ወጥቼ አለፍኩ።

ከዛም ከስዕል ት/ቤት በከፍተኛ ማዕረግ ተመረቅሁኝ።

ባውዛ፦ የስዕል ት/ቤት ቆይታህ እንዴት ነበር?

ወሰኔ፦ የስዕል ት/ቤት ያኔ 5 ዓመት ነበር ማንኛውም ተማሪ 8ኛ ክፍል በላይ የሆነ ተወዳድሮ ካለፈ መግባት ይችላል። ብዙ ጊዜ

የምንስለው የሪያልስቲክ ስዕሎችን ነው ሴትዬዋ እንስራ ይዛ፣ ልጆች ሲጫወቱ ወዘተ ነበር የምንሰራው የስዕል ት/ቤት

በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቄ ከዛ በኋላ ጅማ አስተማሪነት ተመደብኩኛ። ጅማ ሄጄ አላስተምርም ብዬ እዛው አዲስ አበባ

ቆየሁኝ። ስዕል ት/ቤት የተማርኩትን የሪያልስቲክ አሳሳል ጥበብ ትቼ ስዕሎችን በቆዳ ላይ በመሳል መሸጥ ጀመርኩ

የመጀመሪያ አውደርዕዬን ቤልቬዴር የሚባል የስዕል መሸጫ ቦታ ፒያሳ አካባቢ ያለ ነበር እዛ አሳየሁ እና ስዕሎቼንም

ሸጥኩ ከዛም ትልቁ አላማዬ የነበረውን እናቴን በገንዘብ የመርዳት ህልም ማድረግ ችዬ ነበር።

ከስዕል ት/ቤት ከወጣሁ በኃላ ከተለመደው የአሳሳል ውጭ በሆነ የቤተክርስቲያን ስዕሎችን የቀድሞ ይዘታቸውን

እየቀየርኩ መሳል ጀመርኩ፤ ያም ብዙ ተቃውሞ ፈጥሮብኝ ነበር፤ ጊዬርጊስን ከፈረሱ ላይ አውርጄ ስዕል፤ ምርያም እና

ሚኪያኤልን አንድላይ ስስል ብዙ ሰዎች ያን በማድረጌ ተቆጥተው ነበር (ሳቅ) መነን ት/ቤት ስዕል አስተማሪ ሆኜ ለአንድ

ዓመት ከአገለገልኩ በኋላ የተማርኩበት ት/ቤት ስዕል ት/ቤት መመህር አድርጎ ቀጠረኝ Advanced drawing እና

Painting አስተማርኩ።

ባውዛ፦ ሃዋርድ ዩንቨርሲቲ ገብተህ የማስተርስ ዲግሪህን መቀበል ችለሃል የአሜሪካን አገር ትምህርት እና ኑሮ በአሳሳል ጥበብህ ላይ

ምን   አይነት ተፅዕኖ አምጥቷል?

ወሰኔ፦ የሚገርምህ ሀዋርድ ዩኒቨርሲቲ ለመመዝገብ ስመጣ በወቅቱ የሃዋርድ ዩንቨርሲቲ የስእል ት/ቤት ዲፓርትመንት

ሃላፊ ጄፍ ዳናልድሰን የተባለ ሰው ከዚያ በፊት ስዕሎቼን አይቷቸው ያውቅ ነበር እና እንዳውም ት/ቤት መግባት

አያስፈልግህም ሁሉ ብሎኝ ነበር። እኔ ግን መማር ፈለኩ በወቅቱ ዲሲ ታክሲ እየነዳሁ ትምህርቴን መማር ቀጠልኩ፤

ሁለተኛ ዓመት ላይ በመጀመሪያው ዓመት ከፍተኛ ውጤት በማምጣቴ የ ford foundation scholarship

ማግኘት ችዬ ነበር። ጄፍ ዳናልድ ስን አንተ ለምንድን ነው እዚህ መጥተህ እነ ማርያምን እና ጊዎርጊስን አሁንም

የምትስለው    ተዋቸው አለኝ። የአማረኛ ሆህያትን እየቆራረጥኩ እና ቅርፃቸውን እየቀየርኩ የምስለው ነገር ላይ

ለምን   አታተኩርም? የአለም አቀፍ እውቅና ባገኜ መንገድ እንደ ስታይል እነዚህን ስራዎች የሰራ ሰው የለም ብሎ አበረታታኝ

እኔ ደግሞ አኮረፍኩኝ፤ እንዴት የማውቀውን ስዕል ያስተወኛል ብዬ ሳቅ። እኔ መስቀሉ ካልገባ ስዕሌ ስዕል አይሆንም ብዬ

ነው   የማስበው (ሳቅ)። ከዛ በኋላ ለወደፊት መጨወት ጀመርኩ። አሜሪካን ሃገር ከመጣሁ በኋላ አገሬ ናፍቆኝ ነበር

እናቴንም በጣም እናፍቅ ነበር እና አንዳንዴ ለሷ የምፅፋቸው የስዕል ደብዳቤዎች ናቸው እል ነበር ፕሮፌሰሮቼ

ሲጠይቁኝ።  ከዛም ቋንቋዬ ሲደብር ጓደኞች ሲኖሩኝ ኑሮ እየቀለለኝ መጣ የምሰራውንም ስዕል እየወደድኩት

መጣሁ።   ዶናልድሰን እንዳለው ከዛበፊት የአማርኛ ፊደላትን እንደ ስታይል አድርጎ በአለም አቀፍ ደረጃ ያስተዋወቀ ሰው

የለም እኔ ስራዎች የመጀመሪያዎቹ ነበሩ።

ባውዛ፦ የስዕል ስራዎችህ በጣም ትልቅ ዋጋ ያላቸው በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ በሆኑ ሙዝየሞች የስዕል ሰብሳቢዎች እና

ጋለሪዎች ውስጥ ይገኛሉ። ላንተ ትልቅ ስኬት የምትለው ምንድንነው?

ወሰኔ፦ በመጀመሪያ የሀገሬን ቋንቋ ይዤ፤ ከቄስ ትምህርት ቤት የተማርኳቸው ፊደሎችን ወደ አለም አቀፍ መድረክ ማምጣት መቻሌ

እና እነዛ ፊደሎች በአለም አቀፍ ቋንቋ ማቅረብ መቻሌ እንደ ስኬት እቆጥረዋለሁ።

በተለያዬ ቦታዎች መታዬታቸው ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው። እንግዲህ እኔ የምሰራቸውን ስዕሎች እነዚህ ተቆርጠው፣

ተጣመው፣   ረዝመው፣ አጥረው፣ ልብስ ለብሰው፣ እየሮጡ የምታያቸው ፊደላትን በቀጥታ አታነባቸውም ነገር ግን

በ creative art ደረጃ የሚሰጡት ትርጉም አለ እንደ እርት ማንኛውም ሰው ሊያነባቸው ይችላል ተብሎ ስለታመነባቸው

ነው በዚህ ሙያዎች እና ጋለሪዎች ስዕሎቼን የምታገኛቸው።

ባውዛ:- በጣም የምትወደው ስዕልህ የትኛው ነው?

ወሰኔ:_“The Preacher” ይባላል በ ዋሽንግተን ዲሲ ስሚሶኒያን ሙዝየም ነው የሚገኘው::

ባውዛ፦ በስዕል ስራዎችህ ተፅዕኖ የፈጠርካቸው ወይም የአንተን የአሳሳል ጥበብ የተከተሉ ሌሎች ሰዓሊያን አሉ?

ወሰኔ፦ ኢትዬጵያ ውስጥ አሉ አንድ በኃይሉ በዛብህ የሚባል ልጅ አለ ጎበዝ አርቲስት ነው ሌላ መዝገቡ ተሰማ የሚባል ሌላ ደግሞ

ስሙ ጠፋኝ ቤልጄም ውስጥ ያለ ልጅ አለ የማውቃቸው፣ በ1970ዎቹ ነው እንግዲህ እነዚህ ልጆች የኔ ተማሪዎች የነበሩት።

በተረፈ ኢትዬጵያ ውስጥ ከሁለት ዓመት በፊት የታዬ “የፊደል ጨዋታ” የሚባል ኤግዚቢሽን ነበረኝ 30 ስዕል

እና 12 ቅርፃቅርፆችን አሳይቼ ነበር። የሚገርምህ ቅርፃ ቅርፆቹ አየር ጤና ሰፈር ነው የተሰሩት። እነዚህ ብረታ ብረት ቤት

የሚሰሩ ሰዎች ናቸው እየበየዱ የሰሯቸው በጣም ትልልቅ ፊደላት 8-9 ጫማ የሚያክሉ እርስ በርስ ተያይዘው

ተንጠልጥለው   ሲደንሱ የተሰራ ነበር። ይሄ በጣም አስደሳች ነበር።

ባውዛ፦ እዚህ አሜሪካን ሃገር ያለው የዲያስፖራው ኮሚዩኒቲ አሁን በጣም አድጓል። በጣም በዝቷል እና እንደማህበረሰብ

ያለውን ንቃተ   ጥበብ (art consciousness) እንዴት ታየዋለህ?

ወሰኔ፦ የማህበረሰቡ የስነ ጥበብ ንቃት በመጠኑም ቢሆን አድጓል ነው የምለው እእኛ ሀገር ሰዎች ብዙ ጊዜ የስዕል ስራዎችን

መግዛት ባይችሉም ብዙ ጊዜ ለመግዛት ይፈራሉ፤ ውድ ይሆንባቸዋል። አንዳንድ ጊዜ ሀበሾች የስዕል ኤግዚቢሽንኖች

ላይ መጥተው የስዕሎችን ዋጋ ሲያዩ የቤት መግዣ ዋጋ ነው ብለው አስቀውኛል። አሁን ኢትዬጵያ ውስጥ ያሉ የወጣት

ሰዓሊያን ስራዎች ሰዎች እየገዙ ሲመጡ አያለሁ ይሄ በጣም የሚበረታታ ነገር ነው። እነዚህን ወጣት ሰአሊያን የሚስሏቸው

ስዕሎች ዘመናዊነታቸው ከድሮው የክታብ ስዕል ይለያል፤ አዲሲቷን ኢትዬጵያ የሚያሳይ ነው በዋጋም ቢሆን ርካሽ ነው

ስዕል ዝምብለህ ግድግዳ ላይ ለጥፈህ ለማዬት ብቻ ሳይሆን እንደ ኢንቨስትመንት መታዬት አለበት። በአሁኑ ሰኣት

የእነ    ገብረክርስቶስ ደስታን፣ ስራ የእነ እስክንድር በጎስያን የአፈወርቅ ተክሌ ስዕሎችን ገበያ ላይ አታገኝም፤ ዋጋቸውም

በጣም ከፍተኛ ነው። በ dealers በኩል በከፍተኛ ዋጋ ነው የሚሸጡት።

ባውዛ፦ በኢትዬጵያውያን ልጆች በእዚህ አገር ተወልደው ያደጉ ስለ ኢትዬጵያ ባህል፣ ቋንቋ፣ ጥበብ ከማወቅ አንፃር ምን መሰራት

አለበት ትልለህ?

ወሰኔ፦ የሁላችንም መረባረብ ያስፈልገዋል፤ እኛ የእኛን ሰዎች ማወቅ አልቻልንም። ልጆቻችን ሰወቻችን ማወቅ አልቻሉም

የተለያዩ    ታላላቅ ሰዎች አሉን፤ ደራሲዎች፣ ሰአሊዎች፣ ምግብ ሰሪዎች ወዘተ እነዚህ ሰዎች ለማወቅ አጋጣሚውን

መፍጠር አለብን። የዚህ ሀገር ሰዎች ናቸው የኛን ሰዎች ሲያከብሩ የምታየው። ልጆችህ ላይ አገራችሁ ይሄ ነው

ብለህ   አትጭንባቸውም ነገር ግን ከባህሉ ቋንቋም ጋር connect ነው ምታደርጋቸው። ሰዎችን ማክበር ዕውቅና

መስጠት፣  ጋብዝ አዋርድ መስጠት “አንድ ብርሌ” አንድ “ስኔ” አዋርድ መሆን ይችላል። ይሄ ሁሉ እንዲሆን እኛ

ወላጆች  ባህላችንን፣ ታሪካችንን እና ሰዎቻችንን ማወቅ አለብን። ጠጅ ለምንድን ነው ቢጫ ሆኖ የቀረው? ለ

ምንሰማያዊ አይሆንም? ወይም ወይነ ጠጅ ለምን አይሆንም?። አረንጓዴ እንጀራ ለምን አንጋግርም? ይሄ ነገር እኛ

ቀድመን ካላስተዋወቅነው ይወሰዳል። አሁንም እኮ ብዙ ነገራችን እየተወሰደ ነው። ፊደሉም እኮ ሊወሰድ ይችል ነበር፤

ክታብ አለን፣ ጀበና አለን …. ሰዓሊዎቹም ሌላውም ሰው ዝም ብሎ እያያቸው ነው። እኔ በራሴ ከመንገዴ ወጥቼ

ኢትዬጵያን የስዕል ስራዎቼን እንዲያዩ አበረታታለሁ እነ “ደ” እና “ቀ” ን ኑ እና ተመለከቷቸው እያልኩ እጋብዛለሁ

እዚህ በኦክላንድ እና በርክሌ በአመት ሁለት ቦታ በፈቃደኛ ሆኜ የሀገሬን ልብስ ለብሼ ባህላችንን አስተዋውቃለሁ።

ባውዛ: በኢትዮጵያ በአሁኑወቅት ስለ አለው የስነጥበብ እድገት ከስዕል እና ቅርጻቅርጸ አንጻር እንዴት ታየዋለህ?

ወሰኔ: በአሁኑ ሰእት ጥሩ እንቅስቃሴ በግላቸው የሚያደርጉ ወጣት ሰአሊያን አሉ:: ጥሩ ስእሎችን ይሰራሉ፣የራሳቸው ይዘት እና

ፈጠራ አላቸው፣ ከድሮው የኛዘመን የክታብ ስዕል ይላያል:: በሌላ በኩል ኢትዮጵያውስጥ አሁንም አንድ የስዕልት/ቤት ነው

ያለው፣ እነዚህ ወጣት ሰአሊያ ንወደ አለም አቀፍመድረክ የሚመጡበት እድል የሚያገኙበት ሁኔታ ጠባብ ነው።

ያሉትችግሮች እንዳሉሆነው በአጠቃላይ ጥሩ እንቅስቃሴ የሚያሳዮ አርቲስቶች አሉ::

ባውዛ: አርቲስት ወሰኔ ውድ ጊዜህን ሰውተህ ለዚህ ቃለምልልሰ ስለተባበርከን በአንባቢወቻችን ስም እጂግ አድርገን እናመሰግናለን::

ወሰኔ እኔም በጣም አመሰግናለሁ::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here