ቋንቋና ባህልን ማወቅ – listen to the interview, Tizita Getie gave to the Voice of Germany on 26th Sept. 2013 on the fesat of Demera.

0
2021
13 year old Tizita Getie (second to the right)
13 year old Tizita Getie (second to the right)

ከሀገር ርቀዉ፤ በተለያየ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የሀገራቸዉን ቋንቋ ባህልና የማንነታቸዉን መለያ ለልጆቻቸዉ እንዴት እና በምን ዘዴ ያወርሳሉ?

አንድ ሰው ማንነቱን ማለት ከመጣበት ወይም ከሚወለድበት ሀገር ፣ የዘር ሀረግ፣ ቤተሰብ ፣ ህብረተሰብ ፣ የሚወርሰውን እንደ ሐይማኖት ፣ሀገር ፣ባህል እና ቋንቋዎች ላሉ እሴቶች ማወቁ እና ማሳወቁ በሚኖርበት አዲስ ሀገር ምን ያህል ፋይዳ ይኖረዋል? የማንነትን መለያ ማወቅ በስብዕና ላይ የሚጫወተዉ ሚና እጅግ ከፍተኛ ነዉ የሚሉንን ኢትዮጵያዊ አባት እና ልጅ የዛሪዉ እንግዳችን አድርገናል።

በጀርመን ተወልዳ ያደገችዉ የ 13 ዓመትዋ ታዳጊ ወጣት ትዝታ ጊቲ ገላዬ ትባላለች። ትዝታ ትምህርቷን በአብዛኛዉ በጀርመንኛ ቋንቋ ብቻ ብትከታተልም አማርኛ ቋንቋን በቤተሰቦችዋ ብርታት በደንብ ለመናገርመብቃትዋን ነግራናለች፤ መናገር ብቻ ሳይሆን መፃፍና ማንበብም ትሞክራለች። ታዳጊዋ ወጣት ትዝታ በምትኖርበት ከተማ ሃንቡርግ ዉስጥ በተደረገ የስነ -ፅሁፍ ዉድድር ተካፍላ አንደኛ ወጥታ መሸለምዋም እዚህ በጀርመን ሀገር ተነግሮላታል።

የትዝታ አባት ዶክተር ጌቲ ገላዬ፤ በሃንቡርግ ዩንቨርስቲ የአፍሪቃ እና የኢትዮጵያ ጥናቶች የትምህርት ክፍል መምህር ናቸዉ።

ከሀገር ርቀዉ፤ በተለያየ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን የሀገራቸዉን ቋንቋ ባህልና የማንነታቸዉን መለያ ለልጆቻቸዉ ማስተማራቸዉ፤ ልጆቹ በሚኖሩበት ሀገር፤ በሙሉ ስብዕና ፤በኩራት ኑሮአቸዉን እንዲገፉ፤ የሀገርንም ምንነት በኩራት መግለፅ እንዲችሉ፤ በትምህርታቸዉም ጠንካራ እንዲሆኑ እንዲቀጥሉ ይረዳቸዋል ሲሉ ከልምዳቸዉ አጫዉተዉናል፤ የለቱን እንግዶቻችን ሙሉ ቃለ-ምልልስ፤ የድምፅ ማድመጫዉን በመጫን ያድምጡ!

http://www.dw.de/popups/mediaplayer/contentId_17116787_mediaId_17116708

Source: www.DW.DE

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here