“ከአቶ መህፉዝ ዩስፍ ሙመድ የRemedy Tax Services እና የMahfuz Insurance Agency ባለቤት ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ…….”

0
1657

ባውዛ፦ በቅድሚያ ለባውዛ ጋዜጣ ቃለ መጠይቅ ፈቃደኛ ሆነህ በመገኘትህ በባውዛ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል እና በአንባብያን ስም ምስጋናዬን እያቀረብኩ ለመግቢያ ያህል ትንሽ ስለራስህ ብታጫውተን።

መህፉዝ፦ እኔም የጋዜጣችሁ እንግዳ እንድሆን ለተሰጠኝ እድል በጣም አመሰግናለሁ። ስሜ መህፉዝ ዩስፍ ሙመድ ይባላል የRemedy Tax Services እና የMahfuz Insurance Agency ባለቤት እና ስራ አርኪያጅ ስሆን ካለፉት ሰባት አመታት በላይ በዚሁ የፋይናንሺያል ሠርቪስ ውስጥ እየሠራሁ እገኛለሁ። ባለትዳርና የአንዲት ሴት ልጅ አባት ነኝ።

ባውዛ፦ ወደዚህ ሙያ እንዴት ልትገባ ቻልክ? ስራውንስ እንዴት አገኘኸው?

መህፉዝ፦ እንግዲህ ወደዚህ ሙያ የገባሁት የሁሉም ነገር መገጣጠም ነው ማለት እችላለሁ። የመጀመሪያም ሆነ ሁለተኛ ዲግሪዬን የተማርኩት በፋይናንስ (Economics) የትምህርት መስክ ነው። ሁሌም ከተሳካ በግል ስራ መተዳደርን እመርጥ ነበር። ስለዚህ ትምህርቱና ፍላጐቱ እንዲሁም በግል ስራ የመተዳደሩ አጋጣሚ ሲስተካከል እኔም ራሴንም ሆነ ማህበረሰቤን በተሻለ ሁኔታ ላገለግልበት በፍላጐትም ልሰራው የምችለው ሙያ መሆኑን ስላመንኩ ቶሎ ብዬ እድሉን ተጠቀምኩበት። ይመስገነው ይኸው እንግዲህ ለማደግና ለመሻሻል ጥረት እያደረግን ነው።

ስራው በጣም የሚወደድ ስራ ነው። በተለይ በፋይናሺያል ዕቅድ፣ በታክስ እና ኢንሹራንስ ማማከር ስራ ዙርያ ለሰዎች ብዙ ነገር ለማማከር ስትጥሪ አንቺም ከተለያዩ ሰዎች በመደበኛ ትምህርት ልትማሪ እማትችይውን በጣም ብዙ ነገሮች ትማሪያለሽ። ከብዙ ሰዎች ጋር ትተዋወቂያለሽ ሙያው rewarding and challenging ነው። መሯሯጥን ይጠይቃል ከተሯሯጥሽ ደግሞ በደንብ መደጐም ትችያለሽ በክፍያ ማለቴ ነው።

ባውዛ፦ በአብዛኛው ጊዜ ወይም በተደጋጋሚ ታክስን በተመለከቱ ህብረተሰቡ የሚፈጽማቸው ስህተቶች ምንድን ናቸው? ቀድሞውንስ ምን ጥንቃቄ መደረግ አለበት?

መህፉዝ፦ በጣም ብዙ ነገሮችን ማንሳት ይቻላል። እኔ ሁሉም ሰው ቢረዳው የምለው የተመላሽ (Refund) እና የታክስ አዘጋጆችን ምርጫ በተመለከተ ነው።

ጥቂት የማይባሉ ሰዎች የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው እንደሚባለው ታክሳቸው እንደፈለገው ቢሠራ እነሱ እሚያዩት የተመላሹ (Refund) መጠኑ ነው። በዚህ ምክንያት በጣም ብዙ ሰዎች ከIRS ደብዳቤ እያገኙ እና ቀደም ላሉት አመታት ለወሰዱት አላግባብ ተመላሽ ብዙ መቀጫ (Penality) እና ወለድ (Interest) ለመክፈል ሲገደዱ እናያለን። ታክስ አዘጋጆች ጋር ስንሔድና ታክሳችን ሲሠራ መጠየቅ ያለብን የተመላሽ መጠኑን ብቻ ሣይሆን እንዴት መጣ ብለን መጠየቅ መቻል ነው። ሰዎች ተመላሽ እንዲያገኙ ማድረግ በጣም ቀላል ነው ህጉን ተከትለን መሆኑ ማወቅ ግን ግዴታ ነው።

ታክስ አዘጋጅ ብዙ ያስመልሣል ስለተባለ መሆን የለበትም እምንሔደው ምን ያህል ህጉን ያውቃል? የIRS መስፈርት ያሟላነው ወይ? የሚለውን ነው ማየት ያለብን ገና አንድ ቦታ ከሚያሠሩ ሰዎች ብዙዎች የIRS ደብዳቤ የሚያገኑ ከሆኑ ያኔ ነው መሸሽ።

ሌላው በተደጋጋሚ ከሚታዩ ስህተቶች ውስጥ የሚመደበው የታክስ መረጃዎቻቸውን በሙሉ ሳያሰባስቡ ታክስ የሚያሠሩና ታክስ ተሰርቶላቸው ካለቀ በኃላ ተጨማሪ W2 ሆነ ሌሎች የተረሳ ዶክመንት አግኘተው የሚጨናነቁ ሰዎችን ይመለከታል።

ታክስ ከማሰራታችን በፊት እና ታክስ አዘጋጅ ዘንድ ከመሔዳችን በፊት መረጃዎቻችን በሙሉ መሟላታቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅብናል።

መረጃዎቻችን በሙሉ እስካሁን ካልደረሱ አሠሪዎቻችን ጋር በመደወል በድጋሚ መጠየቅ፣ አሰሪዎቻችን እንቢ ካሎት ለIRS በመደወል ማሳወቅ እናም እንደመጨረሻ አማራጭ በመጨረሻ paystab ማሠራት ይኖርብናል።

ባውዛ፦ በመረጃ አለማሟላትና በሌሎች ምክንያቶች እስካሁን ያላሰራን ሰዎችስ ካለን ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?

መህፉዝ፦ በተቻለ መጠን ከApril 17 በፊት ለማሠራት መሞከር ካልቻልንም ታክስ አዘጋጆቻችንን የታክስ ማዘጋጃ ተጨማሪ ጊዜ (Extension) በመጠየቅ ቢያንስ የ6 ወር ጊዜ ማግኘት እንችላለን። እዚህ ጋር ተጨማሪ ጊዜው ለታክሱ ማዘጋጃ ነበር እንጂ ከፋዮች ከሆንን የምንከፍለውን ግምት ከExtension ጋር መላክ ይጠበቅብናል።

ባውዛ፦ አንድ ታክስ አዘጋጅ ከሌላው የሚለየው በምንድን ነው?

መህፉዝ፦ አንድ ማወቅ ያለብን ነገር ሁሉም ታክስ አዘጋጅ የሚጠቀመው ተመሣሣይ ህግ ነው። በኔ እምነት የሚለያዩት ለታክስ አዘጋጆች በቂ ጊዜ በመስጠት፣ የሚሠራውን ስራ በማብራራት ከህግ አንፃር ተጠያቂነትን የማያስከትል ስራ የሚሠሩት የትኞቹ ናቸው የሚለው ነው። ስለዚህ ታክስ የሚያዘጋጅላቸው ግለሰቦችም መጠየቅ ያለባቸው ጥያቄ ማን ብር ያስመልሳል፣ ማን ትንሽ ያስከፍላል ሳይሆን የታክስ ስራቸው በትክክል ተነግሮአቸው ነገ ከነገ ወዲያም ሁሌም የሚገኘው ታክስ አዘጋጆች እና IRS ደብዳቤ እንኳን በሚመጣ Defend የሚያረጓችው መሆን አለበት።

ባውዛ፦ ወጪ ስለመደመር ልጠይቅህ። በታክስ ላይ የማይደመሩ ነገሮች ምንድን ናቸው እስከ ምን ያህል መደመር ይቻላል?

መህፉዝ፦ ታክስ አዘጋጆች ሁሌም የምንጠየቀው ጥያቄ ነው። ህጉ ደግሞ ግልፅና የማያሻማ ነው። ከታክስ ስራ ጋር በተያያዘ የሚደመሩ ነገሮች ውስጥ እና አንድ በአንድ የተጠቀሱ ናቸው። ለምሳሌ፦ የህክምና ወጪ፣ የቤት ሞርጌጅ ወለድ (Interest), donation, ለመኪና ለቤት የሚከፈለው property tax, Gift and Charity, ሌሎች ከስራ ጋር የተያያዙ ወጪዎች ለምሳሌ፦ የዩኒፎርም ላውንድሪ፣ ከስራ ወደሌላ ስራ ወይም ትምህርት ቤት ስንገባ የተጠቀምንበት ትራንስፖርት ወጪ ወዘተ ዋናዎቹ ናቸው። አንድ አንዶቹ ግን መጠን (limit) አላቸው።

አንድ አንድ ሰዎች ለቤት ኪራይ፣ ለመኪና ኢንሹራንስ ሌላው ቀርቶ ወደ ሐገር ቤት ለቤተሰብ መርጃ የላከውን ገንዘብ የሚደማመር የሚመለስላቸው ሰዎችና የሚያደማመሩ ታክስ አዘጋጆች አሉ ያበፍፁም ስህተት ነው።

ባውዛ፦ ሌላው በብዛት ስለሚጠየቅ ጥያቄ ልጠይቅህ የተጋቡ ሰዎች ታክሳቸውን አንድ ላይ ማሠራት ወይስ ለየብቻ ማሰራት ይመርጣል፡፡

መህፉዝ፦ የተጋቡ ሰዎች ታክሳቸውን በአንድ ላይ (married filing jointly) ወይም በተናጠል (married filing separately) መሠራት ይችላሉ። ሁሉም የሚስማማበት አንድ ነገር አማራጭ ካልጠፋ በስተቀር አንድ ላይ ማሠራት በጣም ጥሩ ጥቅማ ጥቅሞችን ሊያስገኝልን ይችላል። በተለይ ልጆች ካሉን። የተጋቡ ሰዎች Separately ሲያሰሩ በተለይ ሁላችን የምንጓጓለትና በልጆች ምክንያት የሚገኘው ወፈር ያለ ተመላሽ (earned income credit) ሙሉ በሙሉ እናጣለን፣ የትምህርት ቤት ወጪን መጠቀም አንችልም ሌሎች ብዙ ጉዳቶች አሉት ስለዚህ ባልና ሚስት አንድ ላይ ማሠራት የመጀመርያ ምርጫ መሆን አለበት። ባል ወይም ሚስት የመንግስት ዕዳ ካለባቸው ግን ተመላሽ (Refund) ባለብን ዕዳ መሠረት ሊደርሰን ስለሚችል ለየብቻ ማሠራቱ ሊሻል ይችላል። ታክስ አዘጋጆቻቸው ሁሉን በዝርዝር ሊነግሯቸው ይገባል።

ባውዛ፦ አንድ ግለሰብ ወይም ድርጅት ታክስ ማሠራት ለምን ይጠቅመዋል ካልከፈለስ ምን ችግር ይገጥመዋል?

መህፉዝ፦ እንግዲህ ታክስ መክፈልን በተመለከተ በሁለት መልኩ ማየት እንችላለን። ከስነ-ምግባር (morale) እንዲሁም ከህግ አንፃር ማለታችን በአካባቢያችን የምናየው ሁሉ የመሠረተ-ልማት መንገድ፣ መብራት የመሣሠሉት ነገሮች የሚገነቡት ከኛ ከሚሠባሰበው የቀረጥ ገቢ ነው። ስለዚህ እኛ ታክስ አልከፈልንም ማለት ብዙ ነገሮችን እንዳስተጓጐልን ያመለክታል። ከህግ አንፃርም ማንኛቸውም ግለሰብ ሆነ ድርጅት በግልፅ ታክስ ለመክፈል የማንገደድበት ገቢ ካልሆነ በስተቀር ገቢ እስካገኘን ድረስ ታክስ መክፈል ግዴታ ይሆንብናል። አለመክፈላችን ደግሞ ከሚመጣብን ቅጣት በተጨማሪ በወንጀልም ሊያስከስሰን ይችላል።

ባውዛ፦ ለመሆኑ IRS ታክስ አዘጋጆች ላይም ቁጥጥሩን ጨምሯል የሚባለውስ?

መህፉዝ፦ እውነት ነው እንደበፊቱ ታክስ ቢሮ ከፍተን ለመስራት መስፈርቱ በጣም እየጠበቀ ነው። በተለይ ክፍያ እየተቀበሉ ታክስ የሚያዘጋጅ ማንኛውም ግለሰብ ሆነ ድረጅት የታክስ ማዘጋጃ መለያ ቁጥር ከመውሰዱ ጀምሮ በየአመቱ የመመዘኛ ፈተና መውሰድና ማለፍ ግዴታ እየተደረገ ነው።

ባውዛ፦ ቀደም ሲል እንደጠቀስከው ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት ነህ ቤተሰብ ማስተዳደርና የግል ስራ መስራት እንዴት ነው?

መህፉዝ፦ ለሁሉም ጊዜ ለመመደብ መሞከር። በተለይ ለኔ ቢጤው ለማደግ የሚፍጨረጨር ሰው ለቢዝነሱ ዕድገት በቂ ጊዜ መስጠት ወሳኝ ነው። ነገር ግን በሌላ በኩል በብር ልትሞይ የማትችይውን የቤተሰብ ፍቅር ማጣጣም የግድ ነው። ስለዚህ ሁለቱንም በተቻለ መጠን ጐን ለጐን ለማስኬድ እየተራወጥን ነው።

ባውዛ፦ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ለሚፈልጉ ሰዎች አድራሻችሁንና ስልክ ቁጥራችሁን ብትነግረን

መህፉዝ፦ Remedy Tax Services እና

Mahfuz Insurance Agency

6000 Stevenson Ave. Suite 303

Alexandria, VA 22304

ስልክ 571-287-1139 ሞባይል

703-955-0230

703-212-9131

ባውዛ፦ እናመሰግናለን

 

መህፉዝ፦ እኛም ለተሰጠን ዕድል በጣም አመሰግናሁ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here